ሱዳን፤ አይ ሲ ሲ ዳርፉር ውስጥ ምርመራውን አቋረጠ | ዓለም | DW | 13.12.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

ሱዳን፤ አይ ሲ ሲ ዳርፉር ውስጥ ምርመራውን አቋረጠ

ኔዘርላንድ የሚገኘው ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀንጀል ተመልካች ፍርድ ቤት በእንግሊዘኛ ምኅፃሩ ICC ዳርፉር ላይ የሚፈፀሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን አስመልክቶ ከፍቶት የነበረውን ክስ ማቋረጡን አስታወቀ።

ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀንጀል ተመልካች ፍርድ ቤት፥ከፍተኛ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት እንደተፈፀመበት በሚጠቀሰው የሱዳኑ ዳርፉር ግጭት እጃቸው አለበት የተባሉትን ሰዎች ይዞ ፍርድ ቤት ለማቅረብ የጀመረውን ክስ አቋረጠ። በሱዳን ዳርፉር ጉዳይ ተከፍቶ የነበረው የክስ ሂደት መቋረጡን የገለፁት የፍርድ ቤቱ ጠቅላይ አቃቢት ሕግ ፋታው ቤንሶዳ ዓርብ ዕለት ማምሻውን ኒው ዩርክ በሚገኘው የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ተገኝተው ነው። ቤንሶዳ ምርመራው የተቋረጠበት ምክንያት ዳርፉር ላይ ምንም አይነት ትብብር ባለማግኘታቸው እና ባለፉት 10 ዓመታት ማንም ሰው በወንጀለኛነት ለፍርድ ባለመቅረቡ ነው ብለዋል። ጠቅላይ አቃቢት ሕግ እኢአ በ 2005 ዓም ለ ICC የተላለፉት ክሶች ፤ ተከሳሾችን ፍርድ ቤት የሚያቀርብ ማስረጃዎች ባለመሟላታቸው፤ ስድስት ተከሳሾች አሁንም ድረስ በነፃ እንደሚንቀሳቀሱ አስታውሰዋል። ከተከሳሾቹ መካከል የሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር አል-በሺር ይገኙበታል። ሱዳን አሁን ድረስ የዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች መዳኛ ፍርድ ቤት አባል ሀገር አይደለችም።


ማንተጋፍቶት ስለሺ
ልደት አበበ