ሱዳን በእሥራኤል ላይ የሰነዘረችው ወቀሳ | ዓለም | DW | 25.10.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

ሱዳን በእሥራኤል ላይ የሰነዘረችው ወቀሳ

እሥራኤል በደቡብ ካርቱም የሚገኘውን የሱዳን የያርሙክ የጦር መሣሪያ ፋብሪካን በሚሳይል ደብድባለች ሲል የሱዳን መንግሥት ወቀሳ ሰነዘረ። ትናንት እኩለ ሌሊት ላይ በአንድ ጊዜ በአራት ተዋጊ አይሮፕላኖች በተካሄደው ጥቃት ሁለት የፋብሪካው ሰራተኞች ሲሞቱ በርካቶች መቁሰላቸውን ሱዳን ገልጻለች።

Fire engulf the Yarmouk ammunition factory in Khartoum October 24, 2012. A huge fire broke out after a loud explosion on Tuesday night at the arms factory in Sudan's capital Khartoum, a Reuters witness said. Soldiers blocked roads to the factory where more explosions took place as firefighters tried to contain the blaze, a Reuters reporter at the scene in southern Khartoum said. REUTERS/Stringer (SUDAN - Tags: DISASTER)

የሱዳን የያርሙክ የጦር መሣሪያ ፋብሪካ

የሱዳን መንግሥት ለሰነዘረው ወቀሳ እሥራኤል አስተያየት ከመስጠት ተቆጥባለች። ይሁንና አንድ የእስራኤል ከፍተኛ ወታደራዊ ባለሥልጣን ዛሬ ሱዳንን አደገኛና አሸባሪ ሲሉ ወንጅለዋል ።የእሥራኤል መገናኛ ብዙኃን በሱዳን የያርሙክ ጦር መሣሪያ ፋብሪካ ላይ ስለተጣለው ጥቃትና ለጥቃቱ ሱዳን እሥራኤልን ተጠያቂ ስላደረገችበት ወቀሳ ምን ይላሉ?

በእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር የፖሊሲና የፖለቲካ ና ወታደራዊ ጉዳዮች ሃላፊ አሞስ ጊላድ እስራኤል ጥቃቱን መፈፀም አለመፈፀሟን ተጠይቀው በቀጥታ መለስ ከመስጠት ቶቅጥበዋል ። አሞስ ዛሬ ለእስራኤል ሬድዮ በሰጡት ቃለ ምልልስ ሱዳንን አደገኛ ና አሸባሪ ብለዋል ። አሞስ የሱዳን መንግሥት በኢራን ይደገፋል ከማለታቸውም በላይ የኢራን የጦር መሳሪዎች በበግብፅ ግዛት አድርገው ለሃማስና ለ ለሙስሊም አሸባሪዎች መሸጋጋሪያ መንገድም እያገለገለ ነው ሲሉም ከሰዋል ። የሱዳን ካቢኔ ትናንት ማምሻውን በጉዳዩ ላይ ስብሰባ ቢያካሂድም መግለጫ አላወጣም ። በጥቃቱ ማግስት ትናንት የሱዳኑ ፕሬዝዳንት ኦማር አል በሽር የተገኙበት ፀረ እስራኤል ሰልፍ ተካሂዷል ። ወደ 300 የሚሆኑ ሰልፈኞች አሜሪካን በማውገዝ እስራኤልም ከምድር ገፅ እንድትጠፋ ጥሬ አቅርበዋል ። ሱዳን ትናንት እንዳስታወቀችው እስራኤልን በማንኛውም መልኩ መበቀሏ አይቀርም የሱዳን ማስታወቂያ ሚኒስትር አህመድ ቢላል ኦስማን
« አፀፋውን መመለስ አለብን ፤ ምክንያቱም በጣም በዝቷል ። ይህን ሲያደርጉ አሁን አራተኛ ጊዜያቸው ነው ። እኛም በየትኛውም ቦታ የሚገኙ የእስራኤልን ጥቅሞች የማጥቃት መብት አለን ። በርግጥ እስራኤልን አናጠቃም ። ሆኖም ማጥቃት የምንችልበት መንገድ አለን ። መልሱን የምንሰጥበት መንገድ አለን ። የኛን ሰዎች ገድለዋል ። እንዚህ ነፍሶች ርካሽ አይደሉም ። እናም እንዴት አፀፋውን እንደምንመልስ እናውቃለን ።»
ሚኒስትሩ አክክለው እንዳሉት የተደበደበው ፋብሪካ ባህላዊ የጦር መሣሪያዎችን የሚያመርት ነው ።

ግርማው አሻግሬ

ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ
ሸዋዬ ለገሰ

Audios and videos on the topic