ሱስ አስያዥ ዕፅ እና ክርክሩ | ዓለም | DW | 22.04.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

ሱስ አስያዥ ዕፅ እና ክርክሩ

የሕገ ወጥ ሱስ አስያዥ ዕፅ ንግድና ዝዉዉርን ለመቆጣጠር በርካታ መንግሥትት ከ 40 ዓመታት በላይ ሲያካሂዱ የነበሩትን ጦሩነት አቁመዋል። ይህን ያደረጉበት ምክንያት በዉጊያዉ ምንም ዓይነት ዉጤት ባለማግኘታቸዉና የዕፅ ንግድን ለመከላከል ባነሱት ጦርነት የሟቾች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ ነዉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:29
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
04:29 ደቂቃ

ሱስ አስያዥ ዕፅና ዓለም


የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ካለፈዉ ማክሰኞ ሚያዝያ 11 ጀምሮ የዕፅ ዝዉዉርና ንግድን በተመለከተ የነበረዉን መርሕ ለመቀየር ዉይይት አካሂዶአል።
ሱስ አስያዥ ዕፅ በሕጋዊ መንገድ በሁሉ ቦታ ይገኛል። ለምሳሌ እንደ ቡና፤ የአልኮሆል መጠጥ ሲጃራ እንዲሁም መድኃኒት ዉስጥ ሁሉ ሱስ አስያዥ ዕፅ አለ። እንደ ካናቢስ፤ ሄሮይን እዲሁም ክሪስታል ሜት የመሳሰሉት ዓይነት እፆች ደግሞ ሕጋዊ ካልሆኑት እፆች መካከል ይመደባሉ። በዚሕም ምክንያት የእፅ ንግድ ሕጋዊና ሕገ-ወጥ ተከፍሏል። እፅን በሕገ ወጥ መንገድ ለንግድ ማቅረብ በመከልከሉ ምክንያት ዋጋዉ በጣም እንዲንር ሆንዋል። ምንም እንኳ ዋጋዉ ቢንርም ሰዎች ይህን በሕገ ወጥ የሚሸጥን እፅ ከመግዛት አልተቆጠቡም። እንደ ተመድ ጥናት በጎርጎረሳዊዉ 2014 ወደ 250 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች ይህን ሱስ አስያዥ እፅ ተጠቅመዋል። እንደ ጥናቱ በ16ና 64 ዓመት እድሜ ክልል ከሚገኙ 20 ሰዎች መካከል አንዱ እፅን በሕገ ወጥ መንገድ እየገዛ ይጠቀማል። ይህ በሕገ ወጥ መንገድ የሚሸጠዉ እፅ በጣም ተፈላጊ በመሆኑ ግዙፍ ሕገ ወጥ ገበያን አስፋፍቶአል። የመንግስታቱ ድርጅት ባወጣዉ መረጃ መሠረት የተደራጁ ሕገ ወጥ የእፅ ነጋዴዎች በዓመት እስከ 330 ቢሊዮን ዶላር ድረስ እንደሚያገኙበት ይገምታል። በርካታ ገንዘብ ባለበት አካባቢ ሁሉ ኃይል የቀላቀለ ጥቃትና ሙስና ብዙ ርቆ እንደማይገኝ እሙን ነዉ። ይህ ሁኔታ አንዳንድ ሃገሮችን ከፍተኛ ስጋት ላይ ጥሎአቸዋል።

Autor Don Winslow

ዩኤስ አሜሪካዊዉ ፀሐፊ ዶን ዊንስሎቭ

ስለዚህ የእፅን ንግድ የሚቆጣጠር ፖሊሲ እንደሚያስፈልግ ተመልክቶአል። የእፅ ፖሊሲ ከእድገት ጋርም የተያያዘ ነዉ። ምክንያቱም በብዙ የዓለም ክፍሎች ሕገ ወጥ የእፅ ምርት ኤኮኖሚዉን በማሳደግና ለትናንሽ ገበሬዎች የኑሮ ዋስትናን በመስጠት ትልቅ ሚናን ይጫወታል። የእፅ ንግድ ከጤና ጋርም የተያያዘ ነዉ። ምክንያቱም በብዙ አገሮች የእፅ ሱሰኞች ከሱሳቸዉ እንዲላቀቁ ወደ ሕክምና ከመወሰድ ይልቅ ወደ እስር ቤት ይወረወራሉ። አልያም እፅን የሚወጉበትን መርፊ የሚያድል መረሃ-ግብር ባለመኖሩ የሳንባ ነቀርሳን የ HIV ኤድስ በሽታዎችን ያስፋፋሉ። የእፅ ፖሊሲ የደሕንነት ጥያቄንም ይነካል። የአዉሮጳ ፖሊሶ «Europol» ሚያዝያ ወር መጀመርያ ባወጣዉ ዘገባ የእፅ ንግድ ከሚያስገኘዉ ገቢ 1/3 የተደራጁ ሕገ ወጥ ነጋዴዎች ስለያዙት ብቻም ሳይሆን የሽብርተኛ ድርጅቶችም በእፅ ንግድ ገንዘብ ስለሚያገኙበትም ጭምር ነዉ። እፅን በሚመለከት በዓለም አቀፍ ደረጃ ሲደረግ ባለፈዉ ማክሰኞ የተጀመረዉ ዉይይት ከ 18 ዓመት በኃላ የመጀመሪያዉ ነዉ። ይህን ሦስት ቀን የዘለቀዉን ስብሰባ እንዲካሄድ ያነሳሱት ሃገራት ደግሞ ሚክሲኮ ኮሎምቢያና ጓቲማላ ነበሩ። ሃገራቱ ለ 50 ዓመታት በየጊዜዉ እያደገ የመጣዉን የእፅ ጦርነት ባለማሸነፋቸዉና የብዙ ሰዉ ሕይወት በመቀጠፉ ምክንያት ሁኔታዉ አሳሳቢ ሆኖ ነዉ ያገኙት። በሜክሲኮ ስለሚታየዉ የእፅ ንግድ ጉዳይ ጥናት የሚያደርጉት ዩኤስ አሜሪካዊዉ ፀሐፊ ዶን ዊንስሎቭ ጉዳዩ ምንም እንዳላስደነቃቸዉ ነዉ የሚናገሩት።


«ላቲን አሜሪካ በዓለም አቀፍ ደረጃ የዕፅ ዝዉዉርን ለመከላከል ባለዉ መመርያዎች ከማንኛዉም ሃገር ይበልጥ በደሟ ከፍላለች። በሜክሲኮ ከ 100 ሺህ በላይ ሰዎች ከእፅ ጋር በተገናኘ ተገለዋል። ይህ ቁጥር መሃል አሜሪካ ከሚገኙት ሃገራት ከታየዉ ግድያ በቁጥር ምናልባትም ተመሳሳይ ይሆናል አልያም ይበልጣል። ስለዚህ እነዚህ እዕ አምራች ሃገራት አልያም እፅ የሚተላለፍባቸዉ ሃገራት ናቸዉ ። »
የዩኤስ አሜሪካ ጆን ሆፕኪንስ ዩንቨርስቲ ባካሄደዉ ጥናት መሠረት በአንዳንድ የሜክሲኮ ፊደራል ግዛት ዉስጥ የአንድ ሰዉ የመኖርያ እድሜ በአምስት ዓመት አጥሮአል።


የቀድሞዉ የኮሎምኒያ ፕሬዚዳንት ሴዛር ጋቪራ በጎርጎረሳዉያኑ 1990 ዓ,ም መጀመርያ በስልጣን ላይ በነበሩበት ጊዜ የእፅን ጦርነት ተቃዋሚ ነበሩ። ጋቪራ ለዶይቼ ቬለ በሰጡት ቃለ ምልልስ አሁን አዲስ ርምጃ ይደረግ ሲሉ ይጠይቃሉ።
«ኮሎምቢያ እፅን በተመለከተ ከ 20 ዓመታት በላይ በወታደራዊም ሆነ በሕጋዉ ደረጃ ያላትን ፖሊሲ እያጠናከረች ነዉ። ሃገሪቱ ለደሕንነት የምትመድበዉ በጀት በአሜሪካ ከፍተኛዉ ሲሆን በዚሁ ረገድ ያላት ወታደራዊ የደሕንነት ኃይል በላቲን አሜሪካ ከፍተኛ የሚባል ነዉ።»


ቢሆንም ቅሉ ኮሎምቢያ አሁንም የእፅ ንግድ የሚካሄድባት ቦታ ናት፤ ይህን ለመቅረፍ ያልቆፈርነዉ ጉድጓድ የለም ነገር ግን ያገኘነዉ ፋይዳ የለም፤ ሲሉ የቀድሞዉ ፕሬዚዳንት ሴዛር ጋቪራ ተናግረዋል። ጋቪራ በመቀጠል ዓለም አሁን እፅን መጠቀም እንደ ወንጀለኛ አድርጎ ማየቱን ያቁም ሲሉም ተናግረዋል።


የመንግስታቱ ድርጅት በጎርጎሳዉያኑ 1998 ዓ,ም በሰጠዉ የመፍትሄ ነጥብ ላይ ከእፅ ነፃ የሆነች ዓለምን መፍጠር እንችላለን ይል ነበር። ይህም በቀድሞዉ የተመድ ዋና ጸሐፊ ኮፊ አናን ነበር የተነገረዉ። ኮፊ አናን ዛሬ ይህን የቀድሞዉን ሃሳባቸዉን ቀይረዋል። አናን የካቲት መጨረሻ ላይ «ዴር ሽፒግል» ለተሰኘዉ የጀርመን መጽሔት በሰጡት ቃለ-ምልልስ እፅን መጠቀም ሕጋዊ እንድናደርግ ሲሉ ነዉ የተናገሩት። አናን በፃፉት ሌላ ሰፋ ያለ መረጃ ላይ እንደጠቀሱት እፅን በመቃወም የሚካሄድ ጦርነት ሰዎች ላይ የሚደረግ ጦርነት ነዉ ሲሉ ነዉ ያስቀመጡት። እንደ ኮፊ አናን የማጠቃለያ ግምገማ እፅ የብዙ ሰዎችን ሕይወት አንኮታኩቷል ግን ከመንግሥታት የሚወሰዱ የተሳሳቱ ርምጃዎች ደግሞ ሰዎች ላይ ሰቆቃን አስከትሎአል።


ከእፅ ነፃ ዓለምን መፍጠር የማይዘገን ጉም ሆንዋል። በኒዮርክ በተካሄደዉ ጉባዔ የተካፈሉት የጀርመን የሱስ አስያዥ እፅ ጉዳዮች ተጠሪ ማርሌነ ሞርትለርም ከእፅ ነፃ የሆነ ዓለም መፍጠር የማይቻል ከባድ ጉዳይ ነዉ ሲሉ ነዉ የተናገሩት ።
«ለኛ እዉነታዉን በጥሞና ማየታችን አስፈላጊ ነገር ነዉ። በጎርጎረሳዉያኑ 1998 ዓ,ም ዓለም ከሱስ አስያዥ እፅ ትፀዳለች ተብሎ ነበር። ዓላማዉ ወርቃማ ቢሆንም፤ የሚደረስበት አይደለም። ስለዚህም ቅጣት ሳይሆን የሰዎች ጤንነት ፍፁም ቅድምያ የሚሰጠዉ ጉዳይ ነዉ»


በርካታ ሃገራት እፅን መጠቀም ከወንጀል ነፃ መሆኑን በማሳወቅ በሕግ እንዳያስቀጣ ለማድረግ የተለያዩ ሙከራዎች እያደረጉ ይገኛሉ። ለምሳሌ በኡሯጓይ የተወሰነ ብዛት ያለዉ ካናቢስ የተባለዉን እፅ መሸጥ ወይም ማብቀል ሙሉ በሙሉ ሕጋዊ ሆንዋል። ካናዳም ይህን የኡሯጓይን መንገድ መከተል ትፈልጋለች። ይህ ለሦስት ቀናት የተካሄደዉ የተመ ጉባዔ ለማሳየት የሚፈልገዉ እጽን በተመለከተ የዓለም መንግሥታት የትኛዉን መንገድ መከተል እንዳለባቸዉ ነዉ፤ የተገለፀዉ።


ማትያስ ሃይን / አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሃመድ

Audios and videos on the topic