ሱሪ መልበስ 40 ጅራፍ ያስቀጣል | ኢትዮጵያ | DW | 31.07.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ሱሪ መልበስ 40 ጅራፍ ያስቀጣል

ሱሪ መልበስ አርባ ጅራፍ ያስገርፋል መባሉ የተሰማዉ ከወደ ሱዳን ነዉ።

default

ለሴቶች መብት የቆመችዉ ሉብና አህመድ

ሰሞኑን ፖሊስ ከሚዝናኑበት ስፍራ አስር ሱሪ የለበሱ ሴቶችን ይዟል። ሙስሊም ብቻ ሳይሆን ክርስቲያኖችና ሌላ እምነት ተከታይ የሆኑ የሚገኙባቸዉ እነዚህ ሴቶች አስር አስር ጅራፍ መገረፋቸዉን አዣንስ ፍራንስ ፕረስ ከካርቱም ዘግቧል። ሱሪ ለብሰሻል ተብላ የተከሰሰችዉና ርምጃዎን አጥብቃ የተቃወመችዉ ጋዜጠኛና ለተባበሩት መንግስታትም በመገናኛ ብዜሃኑ ዘርፍ የምታገለግለዉ ሉብና አህመድ፤ በዓለም ዓቀፉ ድርጅት ባልደረባነቷ የሚሰጣትን ያለመከሰስ መብትና ከለላ አሻፈረኝ በማለት ብዙሃን እህቶቿ የሚያማርሩትን ሕግ ለመሟገት ቆርጣለች። ለወትሮዉ ለአረብ ሴቶች መብት ይሟገቱ የነበሩት ምዕራባዉያን የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ሲሆኑ ዛሬ ዛሬ ግን ራሳቸዉ አረባዉያን ሴቶች ለመብታቸዉ መቆማቸዉ መታየት ጀምሯል።

ነብዩ ሲራክ/ሸዋዬ ለገሠ

ሂሩት መለሰ

ተዛማጅ ዘገባዎች