ሰዉ ሠራሽ ማዳበሪያ | ጤና እና አካባቢ | DW | 25.09.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ጤና እና አካባቢ

ሰዉ ሠራሽ ማዳበሪያ

አፈር ለምነቱን በተለያዩ ምክንያቶች ያጣል። ለምነቱን ያጣ አፈር ደግሞ ተፈላጊዉን ያህል ምርት ሊያስገኝ አይችልም። በዚህ ጊዜ ታዲያ ማዳበሪያ በመጠቀም ለምነቱን ለማሻሻልና የሚገኘዉን የምርት መጠን ለማብዛት ይሞከራል።

default

 የማዳበሪያ ዓይነቶችን በሁለት ከፍሎ ማየት እንደሚቻል፤ በአጠቃቀም ረገድ ደግሞ ተገቢዉን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ባለሙያዎች ይገልፃሉ።

ስለማዳበሪያ ሲነገር በቀጥታ የሚገናኘዉ ከመሬት ለምነትና በቂ ምርት ከማስገኘት አቅም ጋ ነዉ። አንዳንድ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ላለፉት ሺ ዓመታት ይህ ጉዳይ አርሶ አደሮችን ሲያሳስብ ቆይቷል፤ አሁንም በተለይ የህዝብ ቁጥር እያደገ ከመሄዱ ጋ በተገናኘ ደግሞ አሳሳቢነቱ ከፍ ብሏል።

Weizenfeld in Arkansas

ዘመናዊዉ ሳይንስ በ19ኛዉ ክፍለ ዘመን አጋማሽ የተጀመሩ ጥረቶች ዛሬ በተለያየ መልኩ የሚመረቱ የማዳበሪያ ዓይነቶችን አስገኝቷል። የመጀመሪያዉ በኖርዌይ እንዱስትሪ ከናይትሮጅን የተቀመመ መሆኑን ነዉ መረጃዎች የሚያመለክቱት።

ሸዋዬ ለገሠ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic