ሰማያዊ ፓርቲ ያቀረበው የመብት ጥሰት ወቀሳ | ኢትዮጵያ | DW | 17.08.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ሰማያዊ ፓርቲ ያቀረበው የመብት ጥሰት ወቀሳ

የሰማያዊ ፓርቲ በዛሬው ዕለት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫው በአዲስ አበባ በእስር በሚገኙ አንድ የብሔራዊ ምክር ቤት አባሉ ላይ እየደረሰ ነው ያለውን የመብት ጥሰት በጥብቅ አወገዘ። የፓርቲው ባለስልጣናት በአቶ አግባው ሰጠኝ ላይ ተፈጽሟል የሚሉትን ጥሰት ማረሚያ ቤቱ እንዲያበቃ አሳስበዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 02:42
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
02:42 ደቂቃ

የአቶ አግባው ሰጠኝ ስጋት

ነሀሴ፣ 2008 ዓም በቂሊንጦ ወህኒ ቤት ላይ በደረሰው የቃጠሎ አደጋ ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት አቶ አግባው ለሕይወታቸው መስጋታቸውን በጋዜጣዊው መግለጫ ወቅት ያስታወቁት የፓርቲው ፕሬዚደንት አቶ የሺዋስ አሰፋ ማረሚያ ቤቱ ጥሰቱን የማያበቃ ከሆነ  ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት እንደሚወስዱት አስታውቀዋል።  

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር

አርያም ተክሌ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic