ሰማያዊ ፓርቲ የጠራዉ ሰላማዊ ሰልፍ | ኢትዮጵያ | DW | 31.05.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ሰማያዊ ፓርቲ የጠራዉ ሰላማዊ ሰልፍ

ሰማያዊ ፓርቲ ባለፉት ሳምንታት ጠርቶ ሲገፋ የቆየዉን ሰላማዊ ሰልፍ የፊታችን እሁድ ለማካሄድ ዝግጅቱ መጠናቀቁን አመለከተ።

ፓርቲዉ በሀገሪቱ ዉስጥ አሉ ያላቸዉ አፋኝ ነገሮች እንዲሻሻሉ ለመንግስት ተደጋጋሚ ጥሪ ማቅረቡን በመጠቆም ፤ በሰልፉ የፖለቲካ እስረኞችና ጋዜጠኞች፤ በሃይማኖታዊ ጉዳይ በማንሳታቸዉ የታሠሩት የሙስሊሙ ማኅበረሰብ የመፍትሄ አፈላላጊዎች እንዲፈቱ ለመጠየቅ መዘጋጀቱን ገልጿል። የፓርቲዉ ሊቀመንበር ኢንጂኒየር ይልቃል ጌትነት ለዶቼ ቬለ እንደገለፁት እሁድ ዕለት በሚካሄደዉ የሰላማዊ ሰልፍ ከመቶ ሺህ ህዝብ በላይ ይሳተፋል የሚል ግምት አለ። የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበርን ባለፈዉ ሳምንት ይካሄዳል ተብሎ ሲጠበቅ ወደዚህ ሳምንት ስለተሻገረዉ  ሰላማዊ ሰልፍስቱዲዮ ከመግባታችን አስቀድሞ በስልክ ጠይቄያቸዋለሁ።

ሸዋዬ ለገሠ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic