ሰመርጃም | ባህል | DW | 12.07.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

ሰመርጃም

የሬጌ ዘፈን የሙዚቃ ድግስ ላይ ያተኩራል። የአፍሪቃን አህጉር፣ባህልና ሙዚቃ ለማስተዋወቅ ዘንድሮም ታዋቂ ዘፋኞች ወደ ጀርመን በኮሎኝ ከተማ በተዘጋጀው 27ኛ የሰመርጃም ብቅ ብለው ነበር።

27ኛው የሰመርጃም የሙዚቃ ድግስ ጀርመን ውስጥ በኮሎኝ ከተማ ሲካሄድ ዘንድሮም በሺዎች የሚቆጠሩ ተመልካቾችና 39 የሙዚቃ ባንዶች ገኝተዋል።

Titel: Summerjam 2012 Schlagworte: Summerjam Wer hat das Bild gemacht?: Lidet Abebe Wann wurde das Bild gemacht?: 6-8 Juli 2012 Wo wurde das Bild aufgenommen?: Köln Zuschauer

ዘንድሮም ተመልካቾች በደስታ እና በአንድነት የሙዚቃ ድግሱን ተመልክተዋል

አፍሪቃ ከጥቁርም ይሁን ከነጭ የሬጌ ሙዚቃ አቀንቃኞች አፍ አልጠፋችም። በተለይም ከቲክን ጃ ፋኮሊ አፍ። ዘፈኖቹ ለአፍሪቃ ሀገሮች ንቅናቄ ትልቅ ሚና ተጫውተዋል። በአንዳንድ አገሮቹም እንዳይዘፈኑ ክልክል ነበሩ። ቲክን ጃ ፋኮሊ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ አምንስቲ ኢንተርናሽናል የተጨቆኑ የኪነ ጥበብ ሰዎች ከሚላቸው መዘርዝር ውስጥ ከቶታል። « አፍሪቃ አህጉራችን ሀብታም ናት፤ እኛ አፍሪቃውያን ግን ደሀ ነን። ይህ ክል አይደለም። ልክ ነው ትላላችሁ? መልዕክቴ ይኼ ነው። ማንም አፍሪቃን ለኛ አይቀይራትም እያለ ይዘፍናል። በሰመርጃሙ ድግስ ላይም ቲክን ጃ ፋኮሊ መልዕክት ነበረው።

« ይህ ዘፈን አፍሪቃን ለመጎብኘት ለሚፈልጉ የሚጋብዝ ነው። ስለ አፍሪቃ ለማወቅ፣ ለመናገር ከፈለጋችሁ ወደ አፍሪቃ ኑ። ጥሩ አቀባበል ይደረግላችኋል። አዎ ኑ ኑ ኑ»

ቲክን ጃ ፋኮሊ ራሱን ለአፍሪቃውያን እንደአምባሳደር ነው የሚመለከተው። ለሰዎች ድምፅ እንደሚሆንም ይናገራል። አቀንቃኙ ለህይወቱ ያሰጋው ስለነበር ከትውልድ አገሩ ኮትዲቯር ተፈናቅሎ ወደ ማሊ መሸሽም ነበረበት። «ያኔ በባግቦ ላይ የተደረገውን የተቃውሞ አመፅ ያልተቃወምኩ ብቸኛ አርቲስት ነበርኩ። በዚህም ምክንያት መንግስት ሊወገድ የሚገባው አማፂ አለኝ» በማለት ቲክን ጃ ፋኮሊ ታሪኩን ገልጿል። ሰመርጃም ላይ በርካታ አፍሪቃውያንን እና የሬጌ ሙዚቃ አፍሪቃውያንን ሲያስደስት በሌላኛው ትልቅ መድረክ የጃማይካው አቀንቃኝ ሾን ፖል ወጣት አድናቂዎቹን በበኩሉ ሲያስጨፍር አመሸ።

ሾን ፖል የሬጌ ልጅ የሂፖፕ ወንድም ሲል ራሱን ይገልፃል። ስላቀረበው ዝግጅት ተጠይቆ ሲመልስ፤ « ጥሩ፣ ግሩም ዝግጅት ነበር። ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ሰመርጃም የመጣሁት 2001 ዓም ነበር። ጥሩ ተሞክሮ ነበር። ወደ ዝግጅቱ የሚመጡት፤ በርግጥም ሙዚቃውን የሚወዱ እንደሆነ ለመረዳት ችያለሁ። ይሳተፋሉ። ይህ ያስደስተኛል። ስለሆነም ከዚያን ጊዜ አንስቶ ብዙ ጊዜ ሰመርጃም ላይ ተገኝቻለሁ። ይህ ከመላው አውሮፓ ዝግጅቴን መጥቼ ለማሳየት የምወደው ቦታ ነው። ምክንያቱም የኮሎኝ ከተማ ደስ ያሰኘኛል። ተመልካቾቹ የሚሆኑትን መመልከት አስደናቂ ነው። ለመጀመሪያ ጊዜ ወደዚህ ስመጣ 12 ሺ የሚሆኑ ታዳሚዎች ነበሩ። ያኔ በጣም ብዙ ነበር። ያንን ማየት ደግሞ አስደናቂ ነበር። አዎ! አሁን ድረስ እወደዋለሁ።»

የሾን ፖል ዝግጅት ላይ የተሰጡት አስተያየቶች የተለያዩ ናቸው። አንዳዶች በጠቅላላው ጥሩ ነበር ሲሉ፤ ሌሎች መድረክ ላይ ሲጫወት ጎበዝ አይደለም ይላሉ። አልፎ አልፎ እንደ ምክንያት የሚነሳው፤ የሾን ፖል የአስም በሽታ ለመድረክ ድክመቱ ምክንያት አይሆንም ይላሉ። ሾን ፖል ወደ ሙዚቃው አለም ከመግባቱ በፊት ዋናተኛ ነበር።

ሙዚቀኛ ናቲ ከአዲሶቹ አቀንቃኞች ተርታ ይሰለፋል። በለንደን ብሪታኒያ ነዋሪ ነው። ከደቡብ አፍሪቃዊ እናቱ እና የጣሊያን ዝርያ ከሆነው እንግሊዛዊ አባቱ የተወለደ ወጣት አቀንቃኝ ነው። ያለፈው አመት« ቼንጅ» ለውጥ የተሰኘ አልበሙሉን በገበያ ላይ አውሏል። በሙዚቃ ድግሱ እንደ ናቲ ወጣት እና አልፎ አልፎም ከሬጌ ዘፈን ጋ የማይገናኙ የኪነ ጥበብ ሰዎች ተገኝተውበታል።

ዝምባዌነውተወልጄ ያደኩትየሚለውናሽ።ከሶስትጓደኞቹጋከብሪታንናመኪናቸውን እየነዱ እንደመጡ ገልፆልኛል። በሰመርጃምላይለ4ኛጊዜ ተገኝቷል። ስለ ዝግጅቱ ሲናገር የዚኛው አመት እንዳለፋት አመታት አልነበረም። ይሁንና ከሌላ አገር ከመጡ ሰዎች ጋ ለመቀላቀል እድል ይከፍታል ይላል። በትክክል ምን ደስ እንዳላሰኘው እንዲገልፅ ጠይቄዋለሁ፤

« አርቲስቶቹን በተመለከተ፤ ካለፉት ሶስት አመታት ጋ ሲወዳደር ያኔ በርካታ ታዋቂ አርቲስቶች ነበሩ፤ በአሁኑ ግን በጣት የሚቆጠሩ ናቸው። ይህ ጥሩ አልነበረም። ይሁንና ያለውን ጭንቅንቅ ከተመለከትሽ በየጊዜው የተመልካቹ ቁጥር እንደጨመረ ነው። ይህ ከዚህ ድግስ ይዘሽው ልትሄጂ የምትችይ ጥሩ ነገር ነው። »

Titel: Summerjam 2012 Schlagworte: Summerjam Wer hat das Bild gemacht?: Lidet Abebe Wann wurde das Bild gemacht?: 6-8 Juli 2012 Wo wurde das Bild aufgenommen?: Köln Besucher Zelte am Rand des Festivalgeländes,

በመቶዎች የሚቆጠሩ ድንኳኖች ሳምንት ቀድመው ተጥለው ሰንብተዋል

ናሽ እንደ ብዙ ተመልካቾችድንኳንጥሎነውየሰነበተው።አንዳንዶች እንደውም ሳምንት ቀድመው ነው የመጡት። ሶስት ቀን በቆየው የሙዚቃ ዝግጅት ላይ በየቀኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተገኝተዋል። የ39 ዓመቱ ቤኒ ማን ወይንም አንቶኒ ሞሰስ ዴቪስ ከኪነ ጥበብ ሰዎች አንዱ ነበር። ቤኒ ማን ፤ ራሱን የሬጌ ዳንስሆል የሙዚቃ ስልት ንጉስ ነኝ ሲል ያሞግሳል። ። ቢኒ ማን ገና በ10 አመቱ የመጀመሪያ የሙዚቃ አልበም አወጣ። በትውልድ አገሩ ጃማይካም ዕውቅናን አገኘ።

የሁለተኛውን የሰመርጃም ምሽት ያደመቀው አንጋፋው የሬጌ አቀንቃኝ በርኒግ እስፒር ነው። ጃማይካዊው በርኒግ እስፒር ዛሬ 67 አመቱ ነው። ግራጫ መልክ የያዙ የተጠቀለሉ ወይም ድሬድ ሎክስ ፀጉሮቹን እያወዛወዘ ዚያዜም እና ሲደንስ አመሸ። በርኒግ እስፒር «ስሌቨሪ ደይስ» እና « አፍሪቃን ፖስት ማን» የመሳሰሉ ዘፈኖቹን ከአስር አመት በኋላ ዳግሞ በሰመርጃም ዝግጅት ላይ አቅርቧል።

የበርኒግ እስፒር አድናቂዎች ብዙ ናቸው። ከነዚህ መካከል ያነጋገርኳቸው የ50 ዓመቷ ሮዛይገኛሉ።አባታቸውላይቤሪያዊእናታቸውደግሞጀርመናዊናቸው።

የሚጠብቁት፤ምናልባት አንዲትፎቶከበርኒግእስፒርጋለመነሳትከቻልኩ ብለው ለሶስትሰዓትከመድረኩ መግቢያ ቁጭብለውይጠባበቁ ነበር። « እዚህ በመገኘቴ ደስታ ይሰማኛል። በጣም ነው የምኮራው፤ ቦብ ማርሌይን ለመተዋወቅ ችዬ ነበር። አንጋፋ ነው። በርኒግ እስፒር እዚህ ላይ ምን ያህል ጊዜ እንደሚገን እኔንጃ ብቻ፤ እሱም ስለአፍሪቃ አስተማሪ ነው።»

በዝግጅቱ ግቢ የተለያዩ የአፍሪቃ ምግቦችን የሚሰሩ ተገኝተው፤ የአገራቸውን ምግብ ሲሸጡ ባህላዊ እቃዎችን ይዘው የቀረቡም አልጠፉም። እኔም ወደ አንዱ ሱቅ ጎራ አልኩ። « ጄፍ እባላለሁ። የተወለድኩት ማርቲኒግ ሲሆን የምኖረው ፈረንሳይ ነው» አሉኝ። ጄፍ የባህላዊ እቃዎች መሸጫ ቤት አላቸው። በሰመርጃም ላይ ሲገኙ የመጀመሪያቸው ነው። ራስ ተፈሪያን ብለው ራሳቸውን የሚጠሩት የቀዳማዊ ሐይለ ስላሴ ተከታይ ናቸው። ገበያተኞችዎ እነማን ናቸው አልኳቸው።

Titel: Summerjam 2012 Schlagworte: Summerjam Wer hat das Bild gemacht?: Lidet Abebe Wann wurde das Bild gemacht?: 6-8 Juli 2012 Wo wurde das Bild aufgenommen?: Köln Ladenbesitzer Jeff,

በሰመርጃም ድግስ ላይ ጄፍ የተለያዩ የባህል እቃዎችን ሲሸጡ ሰንብተዋል

« ብዙ ሰዎች ሎክስ ( የተጠቀለለ ፀጉር)፤ አላቸው ያ ማለት ግን ራስታ ናቸው ማለት አይደለም። ተመልከች። ብዙ ሰዎች አፍሪቃን ይወዳሉ። ያ ማለት ግን አፍሪቃውያን ናቸው ማለት አይደለም። ይህ በጠቅላላ የሚያሳየው የራስ ተፈሪያንን ጥሩ ነገሮችን ነው። አንድ ሰው በትክክል ባህሉን ባያውቅ ግን የራስታ የሆነ ነገርን ቢመርጥ ምንም አይደል። ብዙም አያሳስበንም እኛ የሰውን ጥሩ ጎን ነው የምንወስደው። እንዲህ እንል ነበር። «ራስታ መሆንህን የሚነግር ሌላ ሰው አይደለም፤ ራስታ ከሆንክ ራስህ ታውቀዋለህ።» ስለዚህ ራስታ መሆን ከፈለግሽ ውስጥሽን በሰዎች መሙላት ይኖርብሻል።

ራስ ተፈሪያን ለኢትዮጵያ ፅኑ ፍቅር እንዳላቸው ሲናገሩ ፣በሚለብሱት ሲያሳዩ ይታያል። « አባታችን ኢትዮጵያዊ ነበሩ። ሐይለ ስላሴ ኢትዮጵያዊ ናቸው በመጀመሪያ ነገር ። ሁለተኛ ደግሞ የሰውን ልጅ መሰረት ለማግኘት የት ነው መኬድ ያለበት ኢትዮጵያ። የክርስትና መሰረት ካስፈለገ ሁሉም ሰው ወደ ኢትዮጵያ መሄድ እንደሚያስፈልግ ያውቃል። ስለ ኢትዮጵያኖች ብቻ ሲባል አይደለም። ይህ ሁላ ሌላ ቦታ ቢሆን ኖሮ ያለው ወደ እዛ ቦታ እንሄድ ነበር። አስታውሽ ስለ ኢትዮጵያ ስናወራ ሁሉም ወደ ኢትዮጵያ መሄድ ይፈልጋል።» ሲሉ ጄፍ ይገልፃሉ።

Ziggy Marley - live Auftritt in Köln / Fühligen See, SummerJam Festival 2001, 3. July 2011 Fotorechte: DW / Cristian Ștefănescu

ባለፈው ዓመት ዚጊ ማርሌይ በመድረክ ላይ

በዚህ አመት ዝግጅት የቀዳማዊ ሐይለ ስላሴ ተከታዮች እና የሬጌ ዘፈን አድማጮች ብቻ ሳይሆኑ በርካታ ከአውሮፓ የመጡ ታዳጊዎች ይበዛሉ።ናዲና ማየር ፤ ከጀርመን ከቢሊፌልድ ከተማ ነው የመጣችው። « ጥሩ ነበር። አየሩንም በተመለከተ እድለኞች ነበርን። ምክንያቱም እንደሚዘንብ ነበር የተነገረው። ሁለተኛ ጊዜዬ ነው አሁን። ሰዎቹም ደጎች ናቸው። አርቲስቶቹም ጥሩ ነበሩ። ስሜቱም ጭምር።»

ናዲና ጓደኞቼ ናቸው ካልሄድን ብለው የመጣሁት እንጂ፤ ይህንን ዘፋኝ ማየት እፈልጋለሁ በማለት እንዳልመጣች ነው የገለፀችው። የ 17 ዓመቱ ፓውል ሌትነር አብረውት ከአውስትሪያ ከመጡ ጓደኞቹ ጋ ቆሞ ነው ያገኘሁት። ወደዚህ የመጣነው የሬጌ ሙዚቃን በጣም ስለምንወድ ብቻ አይደለም ይላል።

« ሰላሙን እንወደዋለን። ሁሉም ሰዎች በአንድነት ያከብራሉ። የሬጌ ሙዚቃ በጣም ጥሩ ነው። በቃ በቃላት ለመግለጽ ይዳግታል።»

እንዲህ እያለ ሶስተኛው ቀን ገባ። ከፈረንሳይ ፣ ከጀርመን ፤ ከስዊዲን ከተለያየ ቦታ የመጡ አርቲስቶች ስራቸውን አቀረቡ። ሶስተኛው ቀን ተገባዶ ወደ መጨረሻው ሲቃረብ እስቲቭን ማርሌይ ወደ መድረክ ወጣ። ህዝቡም አብሮት የአባቱን ቦብ ማርሌይ ዜማ «ዋን ላቭን»ተጫወተ።

ልደት አበበ

ሸዋዬ ለገሰ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች