ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ በጎንደርና ደሴ | ኢትዮጵያ | DW | 15.07.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ በጎንደርና ደሴ

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትኅ ፓርቲ ፤«የሚሊዮኖች ድምፅ ለነጻነት »በሚል መሪ ቃል ለ 3 ወራት ያወጣውን የህዝብ ንቅናቄ እቅድ ትናንት በጎንደርና ደሴ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፍ እንዲከናወን በማድረግ ጀመረ። ከትናንቱ ሰልፍ በፊት ፣ ህዝብ ለሰልፍ እንዲወጣ

default

፣ የፓርቲው አባላት ያደረጉት ሰላማዊ የቅሥቀሳ ዘመቻ፣ በገዥው ፓርቲ ወገኖች ልዩ -ልዩ እንቅፋት ተፈጥሮ እንደነበረና ብርቱ ዛቻም ተሠንዛሮ እንደነበረ የሰልፉ አስተባባሪዎች ገልጸዋል። የተጠቀሰው ዓይነት መሰናክል ቢያጋጥምም ፤ የትናንትናው ሰልፍ፤ በሰላም ተጀምሮ በሰላም መደምደሙን ፣የሰልፉ አዘጋጂዎች ለዘጋቢያችን  ለዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር ገልጸውለታል።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ተክሌ የኋላ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic