ሰላማዊ ሰልፍ በጀርመን | ኢትዮጵያ | DW | 12.08.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ሰላማዊ ሰልፍ በጀርመን

ከተለያዩ የጀርመን ከተሞች የተዉጣጡ ኢትዮጵያዉያን በዛሬዉ ዕለት ፍራንክፈርት ከተማ ላይ ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ። ሰልፈኞች የተለያዩ መፈክሮችን እያሰሙ ወደ ሄሰን የራዲዮ እና ቴሌቪዥን ጣቢያ በመሄድም ኢትዮጵያ ዉስጥ እንዲህ ያሉ ክስተቶችን ሲያጋጥሙ ለሌሎች ሃገራት የሚሰጡትን አይነት የዜና ሽፋን እንዲያደርጉ ጠይቀዋል ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:25

የኢትዮጵያዉያን ተቃዉሞ

ከተለያዩ የጀርመን ከተሞች የተዉጣጡ ኢትዮጵያዉያን በዛሬዉ ዕለት ፍራንክፈርት ከተማ ላይ ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ። ኢትዮጵያ ዉስጥ ሰሞኑን በተለያዩ አካባቢዎች ለሰላማዊ ሰልፍ የወጡ ወገኖች ላይ የመንግሥት ኃይሎች ጥይት መተኮሳቸዉ እና ሰዎችን መግደላቸዉ፤ እንዲሁም ብዙዎችን ማሰራቸዉን ያወገዙት ሰልፈኞቹ፤ የቁርጥ ቀን ልጆች ካሏቸዉ ሀገር ቤት ከሚገኙት ወገኖች ጎን መቆማቸዉንም ገልጸዋል። መነሻቸዉን የከተማዋን ዋና የባቡር ጣቢያ ያደረጉት ሰልፈኞች የተለያዩ መፈክሮችን እያሰሙ ወደ ሄሰን የራዲዮ እና ቴሌቪዥን ጣቢያ በመሄድም ኢትዮጵያ ዉስጥ እንዲህ ያሉ ክስተቶችን ሲያጋጥሙ ለሌሎች ሃገራት የሚሰጡትን አይነት የዜና ሽፋን እንዲያደርጉ እንደሚጠይቁም አመልክተዋል። ፍራንክፈርት የተካሄደዉን ሰልፍ ዘጋቢያችን ጎይቶም ቢሆን ተገኝቶ ተከታትሎታል። እሱንና ከአስተባባሪዎቹ አንዱን ቀደም ብዬ በስልክ አነጋግሬያቸዋለሁ።

ጎይቶም ቢሆን

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic