ሰላማዊ ሰልፍ በአዲስ አበባ | ኢትዮጵያ | DW | 22.07.2021
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ሰላማዊ ሰልፍ በአዲስ አበባ

ሕወሓትን የሚቃወም እና የህዳሴውን ግድብ ሁለተኛ ዙር ሙሌት የሚደግፍ ሰልፍ ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ ተካሄደ። በአዲስ አበባ ከተማ የሴቶች እና ወጣቶች ማሕበራት ጥምረት በተጠራው በዚሁ ሰላማዊ ሰልፍ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ የሚገቡ የውጭ መንግሥታት እና ከፋፋይ ሃሳቦችን የሚነቅፉ መልዕክቶችም ተስተጋብተዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:12

ሕወሓትን የሚቃወም እና የህዳሴውን ግድብ ሁለተኛ ዙር ሙሌት የሚደግፍ ሰልፍ በአዲስ አበባ ተካሄደ

ሕወሓትን የሚቃወም እና የህዳሴውን ግድብ ሁለተኛ ዙር ሙሌት የሚደግፍ ሰልፍ ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ ተካሄደ።በአዲስ አበባ ከተማ የሴቶች እና ወጣቶች ማሕበራት ጥምረት በተጠራው በዚሁ ሰላማዊ ሰልፍ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአሸባሪነት የፈረጀውን ሕወሃትን የሚቃወሙ እና በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ የሚገቡ የውጭ መንግስታት እና ከፋፋይ ሃሳቦችን የሚነቅፉ መልዕክቶች ተስተጋብተዋል። ሁለተኛው ዙር የህዳሴ ግድብ ሙሌት በስኬት መጠናቀቁን በተመለከተ የደስታ መግለጫ መልዕክቶችን ያነገቡ ሰልፈኞችም ታይተዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ሰልፉን  “ለአገር ክብርና ሉዓላዊነት የመቆም ፅኑ ፍላጎት” ብለውታል። የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ስዩም ጌቱ በሰልፉ ስነስረዓት ላይ ታድሞ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።

ስዩም ጌቱ

ታምራት ዲንሳ

ኂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic