ሰላማዊ ሰልፍ በበርሊን  | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 22.02.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አውሮጳ/ጀርመን

ሰላማዊ ሰልፍ በበርሊን 

በዛሬዉ ዕለት ኢትዮጵያዉያን በጀርመን ዋና ከተማ በርሊን ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚካሄደዉን ሕዝባዊ አመፅ በመደገፍ ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ። ከተለያዩ የጀርመን ከተሞች የተዉጣጡት ተሳታፊዎች መገኘታቸዉን ለዶቼ ቬለ የገለፁት የሰልፉ አስተባባሪ በሀገሪቱ የተደነገገውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅም እንደሚቃወሙ አመልክተዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:34

«የአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ አምባገነኖችን መርዳት ያቁም»

ለኢትዮጵያ መንግሥት የተለያዩ ድጋፎች የሚያደርገዉ የጀርመን መንግሥትም አዋጁ እንዲነሳ እንዲጠይቅ፤ እንዲሁም ከአዉሮጳ ሃገራት ጋር በምስጢር ተደርጓል ያሉት ስደተኞችን ወደኢትዮጵያ የመመለስ ስምምነትም ተግባራዊ እንዳይሆን እንዳሳሰቡም አስረድተዋል። ሰልፉን በስፍራዉ ተገኝቶ የተከታተለዉ ይልማ ኃይለ ሚካኤል ተሰላፊዎቹን አነጋግሮ ዘገባ ልኮልናል። 

ይልማ ኃይለሚካኤል

አዜብ ታደሰ

ኂሩት መለሰ
 

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች