ሰላማዊ ሰልፍ በሀዋሳ  | ኢትዮጵያ | DW | 21.02.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ሰላማዊ ሰልፍ በሀዋሳ 

ከሀዋሳና ከሲዳማ ዞን አጎራባች ወረዳዎች በመነሳት በከተማዋ ስታዲየም የተሰበሰቡት ሰልፈኞች ለክልላዊ መዋቅር ጥያቄው ምላሽ ይሰጣል የተባለው ህዝበ ውሳኔ በአፋጣኝ ገቢራዊ እንዲሆን ጠይቀዋል፡፡

ዛሬ ሀዋሳ ውስጥ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ነዋሪዎች የሲዳማ ህዝብ ያቀረበው የክልል መዋቅር ጥያቄ በአፋጣኝ ተግባራዊ ይሁንልን ሲሉ በሰላማዊ ሰልፍ ጠየቁ፡፡ ከሀዋሳና ከሲዳማ ዞን አጎራባች ወረዳዎች በመነሳት በከተማዋ ስታዲየም የተሰበሰቡት ሰልፈኞች ለክልላዊ መዋቅር ጥያቄው ምላሽ ይሰጣል የተባለው ህዝበ ውሳኔ በአፋጣኝ ገቢራዊ እንዲሆን ጠይቀዋል፡፡ ዛሬ ከተካሄደው ሠልፍ ጋር ተያይዞ ሁከትና ግርግር ሊነሳ ይችላል በሚል ሥጋት በከተማዋ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች እና የንግድ ተቋማት በከፊል ተዘግተው ውለዋል፡፡ ይሁንእንጂ የሰልፉ መረሃግብር በሰላማዊ መንገድ መጠናቀቁን ነው የተነገረው ፡፡ ሰላማዊ ሰልፉን የተከታተለው የሀዋሳው ወኪላችን ሸዋንግዛው ወጋየሁ ተከታዩን ዘግቧል፡፡

ሸዋንግዛው ወጋየሁ

ኂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ


 

Audios and videos on the topic