“ርዕዮት” ሬድዮ እና የፖለቲካ ተዋስኦ | ዓለም | DW | 29.01.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

“ርዕዮት” ሬድዮ እና የፖለቲካ ተዋስኦ

ከዋሽንግተን ዲሲ የሚሰራጨው “ርዕዮት” የተሰኘው የኢንተርኔት ሬድዮ ትላንት ጥር 20 የተመሰረተበትን አንደኛ ዓመት በአሜሪካ አክብሯል፡፡ “ርዕዮት” አጀንዳዎችን ቀርጸው ውይይቶችን ከሚያስተናግዱት መካከል የኢንተርኔት ሬድዮዎች እና ፖድካስቶች መካከል ተጠቃሽ ነው።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:18

“ርዕዮት” ሬድዮ እና የፖለቲካ ተዋስኦ

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በበየነ መረብ (ኢንተርኔት) አማካኝነት በተለይም በዩ-ቲዩብ እና በፌስ ቡክ አማካኝነት የሚሰራጩ የኢንተርኔት ሬድዮዎች እና ፖድካስቶች በሀገር ቤትም ሆኑ በውጭ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዋነኛ የመረጃ ምንጭ መሆን መጀመራቸውን ተጠቃሚዎች ይመሰክራሉ፡፡ እነዚህ የመገናኛ ብዙሃን በሀገር ቤትም ሆነ በውጭ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን መካከል የተለያዩ የውይይት እና የክርክር ሀሳቦችን በማጫር እና በማቅረብም ይታወቃሉ፡፡ አጀንዳዎችን ቀርጸው ውይይቶችን ከሚያስተናግዱት መካከል “ርዕዮት” የተሰኘው እና ከዋሽንግተን ዲሲ የሚሰራጨው የኢንተርኔት ሬድዮ ተጠቃሽ ነው፡፡ ርዕዮት ትላንት ጥር 20 የተመሰረተበትን አንደኛ ዓመት በዚያው በአሜሪካ አክብሯል፡፡ የዋሽንግተኑ ወኪላችን ናትናኤል ደበበ የሬድዬውን መስራቾች እና ባለሙያ አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ።

ናትናኤል ደበበ

ተስፋለም ወልደየስ

ሂሩት መለሰ 

   
 
 

Audios and videos on the topic