ራያ እና ሽረ በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት መያዛቸውን የክልሉ መንግሥት አረጋገጠ | ኢትዮጵያ | DW | 18.11.2020
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ራያ እና ሽረ በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት መያዛቸውን የክልሉ መንግሥት አረጋገጠ

የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደብረፅዮን ገብረ ሚካኤል በሰጡት መግለጫ ራያ እና ሽረ በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት መያዛቸውን አረጋገጡ። ደብረጽዮን "ትግሉ አሁንም ቀጣይ ነው። ገና ነው። ውጊያ ውስጥ ነን" ብለዋል። ከትናንት በስቲያ የአውሮፕላን ጥቃት ያስተናገደችው መቐለ ትናንት እና ዛሬ መረጋጋት እንደታየባት ሚሊዮን ኃይለስላሴ ዘግቧል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 02:01

ራያ እና ሽረ በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት መያዛቸውን የክልሉ መንግሥት አረጋገጠ

የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደብረፅዮን ገብረ ሚካኤል በሰጡት መግለጫ ራያ እና ሽረ በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት መያዛቸውን አረጋገጡ።

ደብረጽዮን "ትግሉ አሁንም ቀጣይ ነው። ገና ነው። ውጊያ ውስጥ ነን" ብለዋል። በትግራይ የተጀመረው ውጊያ አስራ ስድስት ቀናት ሆኖታል።

ከትናንት በስቲያ የአውሮፕላን ጥቃት ያስተናገደችው መቐለ ትናንት እና ዛሬ መረጋጋት እንደታየባት ሚሊዮን ኃይለስላሴ ዘግቧል። ሁሉም የግል እና የመንግሥት ባንኮች ተከፍተዋል። የነዳጅ እጥረት በመኖሩ የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ መቀነስ መጀመሩን የገለጸው ሚሊዮን የስልክ እና የኢንተርኔት ግልጋሎቶች እንደተቋረጡ መሆናቸውን ዘግቧል።

ሚሊዮን ኃይለስላሴ

ኂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች