ሩስያ 11 000 ዜጎቿን ከግብፅ አስወጣች | ዓለም | DW | 08.11.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

ሩስያ 11 000 ዜጎቿን ከግብፅ አስወጣች

ሩስያ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ግብፅ ውስጥ የሚገኙ 11,000 ሀገር ጎብኚ ዜጎቿን አስወጣች። ዛሬ እሁድም ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ ወደ ሀገሩ እንደሚመለስ የሩሲያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አርካዲ ድዎርኮቪችን ዋቢ አድርጎ የሩሲያ ዓለም አቀፍ የዜና ኤጀንሲ (RIA) ዘግቧል።

እንዲሁ 2000 የሚጠጉ የብሪታንያ ሀገር ጎብኚዎች ከግብፅ ሻርም ኤል ሼህ ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ዛሬ ተዘግቧል።ግብፅ ውስጥ ከደረሰው የሩስያ የአውሮፕላን አደጋ በኋላ ሩስያ የግብፅ ሙሉ በሙሉ በራራዎችዋን ላልተወሰነ ጊዜ በመሰረዟ ምክንያት 80,000 የሚጠጉ ሀገር ጎብኚ ዜጎቿ መመለሻ አጥተው ግብፅ ውስጥ ነበሩ። ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ በደረሰው አደጋ በአይሮፕላኑ ውስጥ የነበሩት 224 ተሳፋሪዎች በጠቅላላ ሕይወታቸውን አጥተዋል። ጀርመን እና ሌሎች የምዕራብ ሀገራት የአደጋው መንስኤ ራሱን እስላማዊ መንግሥት ሲል በሚጠራው ቡድን የተፈፀመ የቦምብ ጥቃት ነው ሲሉ ያምናሉ። ግብፅ ውስጥ የሚገኘው የአሸባሪው ቡድን ለደረሰው አደጋ ኃላፊነት ቢወስድም የግብፅ ባለስልጣናት ምንም ማረጋገጫ የለም በሚል ውድቅ አድርገውታል። ቡድኑ ጥቃቱን የፈፀመው ሩስያ ሶርያ ውስጥ ለምታካሂደው የአየር ጥቃት አፀፋ እንደሆነ ቢገልፅም፤ አደጋውን እንዴት እንዳደረሰ አላሳወቀም።

ልደት አበበ

እሸቴ በቀለ