ሩስያ እና ዩኤስ አሜሪካ | ዓለም | DW | 19.09.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

ሩስያ እና ዩኤስ አሜሪካ

የዩኤስ አሜሪካ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ በአዉሮጳ የሚታየዉ የስደተኛ ችግር « የሰብዓዊ ቀዉስ» ነዉ ሲሉ ገለፁ። ዩኤስ አሜሪካ 10 ሺህ የሶርያ ስደተኞችን ብቻ መዉሰድ በመፈለግዋ በቂ እንዳልሆነም ተናግረዋል።

እንድያም ሆኖ ስደተኞችን ወደ ሃገራት ማምጣቱ ብቻ የችግሩ መፍትሄ እንዳልሆነና ችግሩን ከመሰረቱ መፍትሄ ማግኘት እንደሚገባ ተናግረዋል። ኬሪ በለንደኑ ጉብኝታቸዉ በሶርያ የርስ በርስ ጦርነት ከሩስያ ጋር « እስላማዊ መንግሥት» እያለ ራሱን የሚጠራዉን ቡድን በመዋጋት የጋራ አቋም እንዳላቸዉ ገልፀዋል። በሌላ በኩል ሩስያ የአሳድን መንግሥት ወታደራዊ ድጋፍ በመስጠትዋ ሁለቱ ሃገራት የነበራቸዉ የጋራ ወታደራዊ ዉይይት መቋረጡ ይታወቃል። በዋሽንግተን የሚገኘዉ የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር ዛሬ እንዳስታወቀዉ የአሜሪካዉ መከላከያ ሚኒስትር አሽተን ካርተር እና የሩስያ አቻቸዉ ሰርጌይ ሾይጉ ስልክ ተደዋዉለዋል፤ ሁለቱ ሃገራት ዳግም ወታደራዊ ዉይይትን ጀምረዋል። የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ ነገ በርሊን እንደሚገቡ ይጠበቃል።

አዜብ ታደሰ

ልደት አበበ