ሩስያና ቱርክ እርቅ ጀመሩ | ዓለም | DW | 01.07.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

ሩስያና ቱርክ እርቅ ጀመሩ

የሩስያና የቱርክ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ዛሬ ፊት ለፊት ተገናኝተዉ በሁለቱ ሐገራት መካከል ተፈጥሮ የነበረዉ ጠብ መወገዱን አስታወቁ። የቱርክና የሩስያዉ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ዛሬ ሶቼ ሩስያ ላይ ተገናኝተዉ ተነጋግረዋል።

የሩስያዉ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ የቱርኩ አቻቸዉን ሜቭሉት ካቮሱግሉን፤ ሶቺ ሩስያ እየተካሄደ ካለዉ የምጣኔ ኃብት ጉባዔ ጎን ተቀብለዉ አነጋግረዋቸዋል።ባለፈዉ ሕዳር የቱርክ አየር ኃይል ሶርያ ድንበር ላይ ይበር የነበረ የሩስያን ጀት መትቶ ከጣለ ወዲህ የሩስያና የቱርክ ግንኙነት ተቃዉሶ ነበር። ሩስያ ተመቶ የወደቀዉ ጀት አዉሮፕላንዋ ታስቦበት የተፈፀመ የጠብ አጫሪ ድርጊት ነዉ ስትል ቱርክን መወንጀሏ ይታወቃል። በያዝነዉ ሳምንት መጀመርያ የቱርክ ፕሬዚዳንት ራቺብ ታይብ ኤርዶዋን ሃገራቸዉ መታ ስለጣለችዉ የሩስያ ጀት አዉሮፕላን ፑቲንን በደብዳቤ ይቅርታ በመጠየቃቸዉ ዉጥረቱ ረግቧል።የሁለቱ ሃገራት መሪዎች የፊታችን መስከረም ቻይና ላይ በሚካሄደዉ የቡድን 20 ጉባዔ ላይ በግል ይገናኛሉ።

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ