1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ረቂቅ አዋጅ የተዘጋጀበት የሃይማኖት እና ህዝባዊ በዓላት ጉዳይ

ዓርብ፣ መጋቢት 6 2016

በስላም ተጀምረዉ የሚጠናቀቁ የኢትዮጵያ ሀይማኖታዊና ህዝባዊ የአደባባይ በዓላት ከቅርብ ግዜ ወዲህ የመንግስት የፀጥታ ችግር እየሆኑ መጥተዋል፤ በዓላቱን ከሚታደሙት ታዳሚውን የሚጠብቁት እየበለጡ፤ የከተማው መንገድ እየተዘጋ በአብዛኛው አንዳንዴ ከበዓሉ 2 ቀናት በፊት ጭምር እየተዘጋ ለእንቅስቃሴ ፈተና የሚሆንበት ግዜ እየጨመረ መጥቷል ተባለ።

https://p.dw.com/p/4dcjW
በአዲስ አበባ የሚገኝዉ አንድነት ፓርክ
በአዲስ አበባ የሚገኝዉ አንድነት ፓርክ ምስል Azeb Tadesse Hahn/DW

ረቂቅ አዋጅ የተዘጋጀበት የሃይማኖት እና ህዝባዊ በዓላት ጉዳይ


በስላም ተጀምረዉ የሚጠናቀቁ የኢትዮጵያ ሀይማኖታዊ እና ህዝባዊ የአደባባይ በዓላት ከቅርብ ግዜ ወዲህ የመንግስት የፀጥታ ችግር እየሆኑ መምጣታቸዉ ተነገር። በዓላቱን ከሚታደሙት፤ ታዳሚውን የሚጠብቁት እየበለጡ፤  የከተማው መንገድ እየተዘጋ በአብዛኛዉ ከበዓሉ 2 ቀናት በፊት ጭምር እየተዘጋ ለእንቅስቃሴ ፈተና የሚሆንበት ግዜ እየጨመረ መጥቷል ተባለ። ለዚህም በኢትዮጵያ በሚከበሩ የህዝብ እና ሀይማኖታዊ በዓላትአከባበሩን ለመወሰን አዲስ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቶ የቀረበለት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሲወያይበት ቆይቶ ጉዳዩን ለሁለት ቋሚ ኮሚቴዎች መርቶታል። ቋሚ ኮሚቴዎቹ ከሚነጋገሩባቸው ነጥቦች አንዱ የሆንውን በሃይማኖታዊ እና ህዝባዊ በአላት ቀን የሚታየውን ሰንደቅ አላማ በተመለክተ ይሆናል ተብሏል «DW» ያነጋገራቸው የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በበኩላቸዉ በጉዳዩ ላይ የተለያዩ አስተያየቶችን ሰጥተዋል። 
የሀይማኖታዊ እና ህዝባዊ በዓላት ለማክበር ሲውጣ ይህን ልበሱ ያንን አውልቁ ከማለት ይልቅ በዓሉን ስርዓት ማስያዝ ይገባል ሲሉ አስተያየት ሰጭዎች ተናግረዋል። በበዓላት ቀን ስው የፈለገውን ለብሶ ቢወጣ ምንም ችግር የለውም፤ እንዲያውም ያላወቅነውን የምናውቅበት እና የምናይበት ይሆናል ሲሉም አክለዋል። በኢትዮጵያ  የሃይማኖት እና የህዝብ በዓላትን እና አከባበሩን በተመለከተ የአዋጅ መሻሻል ሲደረግ ከ 5 አስርት ዓመታት ወዲህ  የመጀመሪያው ሲሆን አዋጁ ተሻሽሎ ሲወጣ ሀገሪቱ ያሏትን የህዝባዊ በአላትን ቁጥር ከማስቀመጡም በላይ ኃይማኖታዊ እና ብሔራዊ የህዝብ በዓላት ሲከበር የሚታዩ ሰንደቅ አላማ ላይ ወሳኔ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።


ሃና ደምሴ 


አዜብ ታደሰ
ዮኃንስ ገብረግዚአብሔር