ረመዳን በሳዑዲ አረቢያ | ዓለም | DW | 24.05.2020
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

ረመዳን በሳዑዲ አረቢያ

በቅዱስ ከተማዋ መካ የካዕባ መሳጅድና በመዲና የመስጅድ ነበዊ በታሪክ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ረመዳን በራቸውን ለሚሊዮን ምዕመናን ዝግ ሆኖ ከቅዱሳን መሳጅዶች በሚተላለፍ ጸሎት ረመዳን በሰላም ተከውኗል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 07:15

ረመዳን በሳዑዲ አረቢያ

በቅዱስ ከተማዋ መካ የካዕባ መሳጅድና በመዲና የመስጅድ ነበዊ በታሪክ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ረመዳን በራቸውን ለሚሊዮን ምዕመናን ዝግ ሆኖ ከቅዱሳን መሳጅዶች በሚተላለፍ ጸሎት ረመዳን በሰላም ተከውኗል።

 የረመዳን ጾምና ጸሎት በሰላም ማክተሙን ተከትሎ በመላው አለም ለሚገኙ ሙስሊማን ታላቁ የኢድ አል-ፈጥር ክብረ በአል ከመካ ካዕባ የኢድ ሰላት በቀጥታ ስርጭት በማስተላለፍ ተበስሯል።

በሳውዲና በቀረው የአረብ ሀገራት የሚገኙ ኢትዮያውያን በአሉን በሰላም ለመቀበል መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል። በአሉን በሚመለከት ያነጋገርኳቸው ኢትዮጵያውያን የኮሮና ከኮቪድ 19 ስርጭትን ተከትሎ እጅግ በጣም ፈታኝ በሆነ ሁኔታ ያሳለፉት መሆኑን ገልጸውልኛል። ያም ሆኖ የዘንድሮው ረመዳን በኢትዮጵያውያን መካከል የበለጠ መረዳዳትና መደጋገፍን የታየበት የመተሳሰብ የጾምና የጸሎት ወቅት መሆኑን እንዳስደሰታቸው እንዲህ በማለት ያስረዳሉ።

የኮሮና ከኮቪድ 19 ስርጭትን ተከትሎ ሁሉም ነገር በተዘጋጋበት ሁኔታ በተለይም በግል ስራ የሚተዳደሩ ኢትዮጵያውያን ፈታኝ ወቅት እንደነበር ተናግረዋል። በቤሩት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በበኩላቸው በበኩላቸው ባስተላለፉት መልዕክት እንዲህ ብለዋል። የሳውዲ መንግስት እ.ኤ.አ ከነገ ቅዳሜ May 23 (ግንቦት 15) ጀምሮ May 27 (ግንቦት 19) ድረስ ለ24 ሰዓታት የሚፀና አውጥቷል። በወጣው ህግ መሰረት ግብይት ለመፈጸም ግሮሰሪ እና ሱፐርማርኬቶችን የመሰሉ የገበያ ማዕከላት ለ24 ሰዓታት ክፍት ይሆናሉ፣ ። የስጋና አትክልት መሸጫ እንዲሁም የቤንዚን ማደያዎች ከጠዋቱ 12 ሰዓት(6AM) እስከ ቀኑ 9 ሰዓት(3PM) ክፍት ይሆናሉ።

ነብዩ ሲራክ

እሸቴ በቀለ

Audios and videos on the topic