ረመዳን ሙባረክ | ባህል | DW | 27.07.2012
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

ባህል

ረመዳን ሙባረክ

ሐምሌ 13 አርብ በመላዉ አለም የሚገኙ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች የረመዳን ጾም ይጀምራሉ። የእስልምና ሃይማኖት ምሶሶ ከሚባሉት አምስቱ ዋና መሰረታዊ ነገሮች መካከል የረመዳን ጾም አንዱ ነዉ። በጀርመን የሚኖሩ ወደ አራት ሚሊዮን የሚጠጉ ሙስሊሞች በዘንድሮዉ ረመዳን በቀን ወደ 18 ሰአት ያህል መጾም ይኖርባቸዋል።

ነገ አርብ በመላዉ አለም የሚገኙ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች የረመዳን ጾም ይጀምራሉ። የእስልምና ሃይማኖት ምሶሶ ከሚባሉት አምስቱ ዋና መሰረታዊ ነገሮች መካከል የረመዳን ጾም አንዱ ነዉ። በጀርመን የሚኖሩ ወደ አራት ሚሊዮን የሚጠጉ ሙስሊሞች በዘንድሮዉ ረመዳን በቀን ወደ 18 ሰአት ያህል መጾም ስለሚኖርባቸዉ በተለይ ለወጣቶች እና ሰራተኞች ጾሙ እጅግ ከባድ ሳይሆን አይቀርም። በሌላ በኩል የስራ ፈቃድ እርፍት መዉሰድ የሚችል የረመዳንን ጾም የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ በሰፋት በሚገኝበት አልያም ከመጣበት አገር ከዘመድ ወዳጁ ጋር  የጾሙን ስነ-ስርአት በጋራ ይካፈላል። ግን  የረመዳንን ጾም በጀርመን የሚያሳልፉና  በከባድ ስራ ተጠምደዉ የሚዉሉ ሰዎች ምን አይነት መፍትሄን ይፈልጉ ይሆን? ኢትዮጵያዉያንስ ይህን ጾም እንዴት ያሳልፉታል የለቱ ዝግጅታችን የሚዳስሰዉ ነዉ፣

NO FLASH Ramadan Mekka

ማለዳ ጠዋት ጎህ ሳይቀድ ጀምሮ ምሽት እስኪ ጨልም ከ 18 ሰአታት በላይ በየቀኑ ለአንድ ወር ያህል ምግብ አለመብላት፣ ዉሃ አለመጠጣት ነዉ በተለይ በጀርመን አገር ለሚኖር የሃይማኖቱ ተከታይ ጾመኛ። ሃሙስ ለሊት ለነገ አርብ አጥብያ ከንጋቱ 9 ተኩል ላይ የረመዳን ጾም  ይጀምራል። በርግጥም የጾሙ ወቅት እጅግ አስደሳች እና ዉብ ግዜ ነዉ። ቢሆንም ግን ብዙ ፈተናን የሚጠይቅበት ግዜ መሆኑ አጠያያቂ አይደለም። ወቅቱ በተለይ በመሃል አዉሮጳ  በሚገኙ እንደ ጀርመን ባሉ አገራት በጋ እና ከፍተኛ የሙቀት ግዜ በመሆኑ ጾሙን ይበልጥ ፈታኝና ከባድ ያደርገዋል። እጅግ ሞቃታማ በመሆኑ ዉሃ የመጠጣት ፍላጎትም በእጥፍ ድርብ ይጨምራል። ድካም እና የመዛል ስሜት ከሚታየዉ ከፍተኛ ሙቀት በተጨማሪ በጾም ወራት የሚታይ እና የተለመደ ነዉ። የሲጋራ ሱስ ያለባቸዉ አንዳንድ ጿሚዎችም የጾም ወቅት እጅግ ረጅም በመሆኑ ሲቸገሩ ይታያል።  ኢትዮጵያዉያንን አነጋግረናል ሙሉዉን ዝግጅት ያድምጡ!

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሀመድ

Audios and videos on the topic

 • ቀን 27.07.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/15ams
 • ቀን 27.07.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/15ams