ረመዳንን የሚጾሙ ወጣቶች | ባህል | DW | 11.07.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ባህል

ረመዳንን የሚጾሙ ወጣቶች

ለመሆኑ ወጣቱ ፆሙን እንዴት ይጾማል? ያፈጥራልስ? የረመዳን ጾም ከገባ ሁለት ሳምንት ሊሞላው ጥቂት ቀናት ነው የቀሩት። በዚህ በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በፆም ፀሎት የሚታሰበው የቅዱስ ወር ለማን ም ሙስሊም ቢሆን ግዴታ ነው።

የሆነው እንዳለ ሆኖ ለሰው ልጅ መኖር ወሳኝ ከሆነው ነገር አንዱ ደግሞ መመገብ ነው። ነገር ግን ለአንድ ወር ያክል ምግብና መጠጥ ቀኑን ሙሉ መከልከል፤ ቃሉ በመጀመሪያ ደረጃ ከባድ እና አሰልቺ ሊያደርገው ይችላል። ነገር ግን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሙስሊሞች በቀን ለረዥም ሰዓታት በፍቃደኝነት ከመመገብ ለመቆጠብ እና ለመፆም ይወስናሉ። ሙስሉም ወጣቶች የፆሙን ጊዜ እንዴት ያሳልፋሉ። ነቢል አህመድ የ4ኛ ዓመት የኢንጂነሪንግ ተማሪ ነው። ፆም እስካሁን ጥሩ ነው ይላል። በተለይ ረመዳን እሱን መሰል ወጣቶች ዘንድ ምን እንደሚመስል እና ፆሙ እንዴት እንደሚጠቅም አብራርቶልናል።

ነኢማ መሀመድ ከነቢል ጋር አንድ ኮሌጅ ነው የምትማረው። ረመዳን መፆም መቻሏ ትልቅ ደስታ ፈጥሮላታል።ነኢማ ከቤተሰቦቿ ጋር ነው የምታፈጥረው። አንዳንዴ ግን በሰዓቱ እቤት ለመድረስ አይሳካላትም። ቢሆንም ግን ብቻዋን መንገድ ላይ ማፍጠሩን አትመርጥም። ነኢማ ቤት ውስጥ ያለውን ለመፍጠሪያ የታሰበውን በማብሰሉ ረገድ እተባበራለሁ ትላለች። ነቢልም ከትምህርት ቤት መልስ ወደ ቤቱ ሄዶ ከቤተሰቦቹ ጋር ነው የሚያፈጥረው።

ሌላው በጀርመን ነዋሪ የሆነው አኑዋር ሙፍታር ነው። የረመዳን ፆም በጀርመን ምን ከባድ እንደሚያደርገው፤ ወይም ከባድ ነው እንደሚባል ገልፆልናል።

በረመዳን ወቅት እያንዳንዱ ሙስሊም መጾም እንዳለበት ቁራን ቢደነግግም ለመፆም የማያስገድድም ፍቃድ አለ። ለምሳሌ የታመሙ፣ እርጉዝ ወይም እመጫት የሆኑ ሴቶች እና ለጉርምስና ያልደረሱ ልጆች አይገደዱም። ከዚህም ሌላ በስራ በጤና ወይም በሌላ ምክንያት በዚህ የረመዳን ወቅት መፆም ያልቻለ ወይም ፆሙን ያቋረጠ ሙስሊም የተቋረጡትን ቀናት ሌላ ጊዜ መፆም ይኖርበታል። ነቢል በትምህርት ቤት የፈተና ወቅት መፆሙ ፆሙን እንዲያቋርጥ አላስገደደውም ነገር ግን በወር አበባ ጊዜ ጾሙን ማቋረጥ ግድ የሚሆንባት ነኢማ ምንም እንኳን በዚህ ወቅት መመገብ ቢፈቀድላትም፤ ሌሎች ሳይበሉ እሷ ብቻዋን መመገብ ይከብዳታል።

በኢትዮጵያ እና ጀርመን የሚገኙ ሶስት ኢትዮጵያውያን የረመዳንን ፆም እንዴት በፆም በፀሎት እንደሚያሳልፉ ማወቅ ከፈለጋችሁ የድምፅ ዘገባውን ተጫኑ።

ልደት አበበ

ነጋሽ መሀመድ

Audios and videos on the topic