ሥደተኞች እና የጀርመን ምርጫ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 10.09.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

ሥደተኞች እና የጀርመን ምርጫ

አብዛኞቹ ስደተኞች ከሁለቱ ትላልቅ ፓርቲዎች ከሶሻል ዴሞክራቲኩ ፓርቲ (SPD) እና ከክርስቲያን ዴሞክራቲክ ሕብረት አንዱን ይመርጣሉ።የጀርመን የምጣኔ ሐብት ጥናት ተቋም የስደተኞች ጉዳይ አጥኚ ኢንግሪድ ቱቺ እንደሚሉት ከሁለቱ አንዱን የመምረጡ ዝንቤላ ደግሞ በየፖለቲካ ፓርቲዎቹ መርሕ እና በየስደተኛዉ ዳራ ላይ የተመረተ ነዉ።

ARCHIV - Eine türkische Wählerin mit Kopftuch gibt am 17.09.2006 in Berlin ihre Stimme ab. Rund 2,43 Millionen Berliner waren aufgerufen, über die Zusammensetzung des Senats bis 2011 zu entscheiden. In Deutschland lebten 2008 rund 15,4 Millionen Menschen mit ausländischen Wurzeln. Davon haben 8,1 Millionen (9,9 Prozent der Bevölkerung) einen deutschen Pass und dürfen wählen. Foto: Gero Breloer dpa (zu dpa-Themenpaket Migranten und Wahlen 2009 vom 01.06.2009) +++(c) dpa - Bildfunk+++

በምርጫ-2009

የፊታችን መስከረም አጋማሽ ጀርመን በሚካሔደዉ ምርጫ ከአምስት ሚሊዮን የሚበልጡ ስደተኞች ወይም የዉጪ ዝርያ ያላቸዉ ጀርመናዉያን የመምረጥ መብት አላቸዉ።በምርጫዉ መሳተፍ አለመሳተፋቸዉ የሚወሰነዉ ግን በስደተኝነት ዳራቸዉ ማለት ለመምረጥ የሚያስችላቸዉን ሠነድ (ዜግነት) በማግኘት፥ አለማግኘታቸዉ ነዉ።ከዚሕም በተጨማሪ እድሜያቸዉ ለመምረጥ የሚበቃ መሆን አለበት፥ የመምረጥ መብታቸዉ በጤና ወይም በሌላ ሕጋዊ ምክንያት ያልተገፈፈ መሆኑም ሊረጋገጥ ይገባል።የመምረጥ ፍላጎቱም መታከል አለበት።ናኦሚ ኮንራድ የዘገበችዉን ነጋሽ መሐመድ እንደሚከተለዉ አጠናቅሮታል።


በርሊን የመጣበትን ምክንያት ሲጠየቅ፥ «ፍቅር» ይላል ዮአን ዲያትስ እየተፍለቀለቀ።በዘንቀ-ብዙ ነዋሪዎችዋ የተዥጎረጎረችዉን በርሊንንም (የሚያፈቅራትን ቆንጆ ያክል) ባይሆንም ለመዉደድ፥ ለመመልመድ ጊዜ አልፈጀበትም።ወላጆቹ ከኩባ ሚያሚ-ዩናይትድ ስቴትስ የተሰደዱ ኩባዉያን ናቸዉ።እሱ አሜሪካዊ።ቅይጥ-ማንነት።የዛሬ ሰባት ዓመት ግድም ሌላ ጨመረበት። ጀርመናዊነትን። ምክንያት?

«ምክንያቱም የመወሰን መብት እንዲኖረኝ በመፈለጌ ነዉ።መራሔ-መንግሥት ወይም የምክር ቤት እንደራሴ መምረጥ እፈልጋለሁ።በፊት አይፈቀድልኝም ነበር።»

Die 18-jährige Kurdin Hamsey Bayram (Mitte) erlernt an der Berufsfachschule Paulo Freire in Berlin gemeinsam mit anderen Migranten den Beruf der Sozialassistentin. Bilder für den Beitrag Berufsfachschule Paulo Freire bildet Migranten zu Sozialassistenten aus für Studi-DW Die Bilder sind von Bianca Schröder am 24.4.2013 in Berlin aufgenommen.

ትዉዉቅየጀርመን መንግሥት የዛሬ ሁለት ዓመት ይፋ ባደረገዉ ጥናት መሠረት እንደ ዲያትስ ሁሉ ጀርመን ዉስጥ 16 ሚሊዮን ስደተኞች እና የስደተኛ ዝርያ ያላቸዉ ሰዎች አሉ።ለመምረጥ ወይም ለመመረጥ ግን አድም እድሜያቸዉ ባለመድረሱ፥ አለያም ጀርመናዊ ዜግነት ሥለሌላቸዉ አብዛኞቹ አይችሉም።መምረጥ የሚችለዉ የጀርመን ፓስፖርት ማለት ዜግነት ያለዉ ብቻ ነዉና

የአዉሮጳ ሕብረት አባል ሐገራት ዜጎች ግን ከሌሎቹ ለየት ያለ መብት አላቸዉ።ለከተማ መስተዳድር እና ለአዉሮጳ ምክር ቤት በሚደረገዉ ምርጫ ድምፅ የመስጠት መብት አላቸዉ።ለጀርመን ምክር ቤት ግን እነሱም ቢሆኑ መምረጥ አይችሉም።

ከተቀረዉ ከአስራ-ስድስት ሚሊዮኑ የመምረጥ-መመረጥ መብት ያለዉ አንድ አምስተኛ ያሕሉ ነዉ።ከነሱም መሐል ድምፁን የማይሰጥ አለ።አምና የተደረገ ጥናት እንዳመለከተዉ ከአራት ዓመት በፊት በተደረገዉ ምርጫ መምረጥ ከሚችለዉ ስደተኛ ድምፁን የሰጠዉ 72.3 በመቶዉ ነዉ።ከአጡራዉ ጀርመናዊ ግን 81.5 ከመቶዉ መርጧል።የዉጪ ዝርያ ያለዉ ወደ ምርጫ ጣቢያ የማይሔድበት ምክንያት የተለያየ ነዉ።ዋናዉ ግን አንድም የልምድ አለያም የፍላጎት ማነስ ነዉ።ዲያትስ ይሕን ሲሰማ ጭንቅላቱን ይነቀንቃል።«መሆን የለበትም» እንደማለት።

«አሜሪካ እንደሚሆነዉ በፖስታ ሳጥኔ ዉስጥ የድምፅ መስጪያ ካርድሕ ይኸዉልሕ፥ እና ምረጥ ሥባል ፌዝ ይመስለኛል።መምረጥ ዴሞክራሲያዊ መብትሕ ነዉ።አሜሪካ አሁንም ድረስ ለምርጫ በመመዘግብ ጉዳይ እየተወዛገብን ነዉ።እዚሕ በፍላጎት ነዉ።አሜሪካ ግን መንጃ ፍቃድ ለማገኘት ስታመለክት «ለምርጫ እንመዝግብሕ» እያሉ ይነዘንዙሐል።»

የፖለቲካ ፓርቲዎችን በመደገፉ ረገድ አብዛኞቹ ስደተኞች ከሁለቱ ትላልቅ ፓርቲዎች ከሶሻል ዴሞክራቲኩ ፓርቲ (SPD) እና ከክርስቲያን ዴሞክራቲክ ሕብረት አንዱን ይመርጣሉ።የጀርመን የምጣኔ ሐብት ጥናት ተቋም የስደተኞች ጉዳይ አጥኚ ኢንግሪድ ቱቺ እንደሚሉት ከሁለቱ አንዱን የመምረጡ ዝንቤላ ደግሞ በየፖለቲካ ፓርቲዎቹ መርሕ እና በየስደተኛዉ ዳራ ላይ የተመረተ ነዉ።


BERLIN, GERMANY - MAY 16: German Chancellor Angela Merkel greets students at the Sophie Scholl school during a visit on the fifth European Union school project day on May 16, 2011 in Berlin, Germany. The nationwide initiative is meant to foster a stronger understanding young people of the role of the European Union. (Photo by Sean Gallup/Getty Images)

ሜርክል ከዉጪ ተወላጆች ጋር

«ባጠቃላይ ሲታይ፥ ቀድሞ እንግዳ ሠራተኞች የመጡባቸዉ ሐገራት ተወላጆች በልማዱ ለሠራተኛዉ መደብ የቆመዉን SPDን ወደ መምረጡ ያዳላሉ።ዘግየት ብለዉ ከምሥራቅ አዉሮጳ ወደ ጀርመን የተመለሱ (የጥንት) ጀርመናዉያንና ከዚያ የፈለሱ ስደተኞች ባንፃሩ ወደ CDU ማዘንበሉን ይመርጣሉ።የዚሕ አይነት አቅጣጫ አለ።»


የአረንጓዴዎቹ ፓርቲም ተወዳጅ እየሆነ ነዉ።በተለይ የስደተኞቹ ሁለተኛ ትዉልድ ማለት ከስደተኞቹ ወይም ከፈላሾቹ ቤተ-ሰቦች ጀርመን ተወልደዉ ካደጉት አስራ-ሥምንት ከመቶ ያሕሉ ከትላልቆቹ ፓርቲዎች ይልቅ አረንጓዴዉን ይመርጣሉ።ያም ሆኖ ሁለቱ ትላልቅ ተቀናቃኝ ፓርቲዎች ባጠቃላይ ከዉጪ ተወላጅ የአርባ ከመቶዉን ድጋፍ እንደያዙ ነዉ።

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ


Audios and videos on the topic