ሥዕላዊ ጥበብ እና ኢትዮጵያ | ባህል | DW | 07.07.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

ሥዕላዊ ጥበብ እና ኢትዮጵያ

የሥዕል ጥበብን እዉቀትና ክሂል ማስተማር በራሱ እንደጋና መማር ነዉ። በሥዕላዊ ጥበብ የካበተን አእምሮአዊና አካላዊ ልምድ ለወጣት ሠዓሊ ተማሪ ማስተላለፍ ማቀበልና ማዉረስ ራሱን የቻለ ሙያ የሚፈልግ ታላቅ ሃላፊነት ነዉ።

default

ሙዚቃ ቋንቋ ነዉ እንደምንለዉ ሁሉ፣ በሥዕልም ስሜታችንን መግለጽ በመቻላችን ሥዕል ቋንቋ መሆኑን እናረጋግጣለን። በስነ-ጥበብ ኢትዮጽያ ጥንታዊ ቱፊት አላት። ዛሪ በኢትዪጽያ ቱሪስቶች የሚጎበኙት ቦታዎች አንዱ ያለፈዉ ትዉልድ በስነ-ጥበብ፣ በኪነ-ህንጻ ክህሎቶቱ በተወልን አሻራ ነዉ። በኢትዮጽያ በስነ-ጥበብ ማለት በሥዕል ረገድ ምን ያህል እንቅስቃሴ አለ። በኢትዮጽያ አቆጣጠር 2000 አ.ም በህጋዊ ፈቃድ አብራሄ ጥበብ ደብር አልያም ኢላይትመንት አርት አካዳሚ በሚል መጠርያ የተቋቋመዉ የስዕል ትምህርት ቤት እስከ አሁን ሃያ አምስት ተማሪዎችን አስመርቆአል። የኢላይትመንት የስዕል  አካዳሚ አንዱ መስራች እና የስዕል አስተማሪ አቶ እሸቱ ጥሩነህ ስለ ስስዕል  ትምህርት ቤቱ ማብራርያ ይሰጡናል። 
የሥዕል ጥበብ ዕይታዊ ቋንቋ፣ ምስላዊ እሳቤ እንዲሁም ሥዕላዊ መግለጫ ነዉ በማለት ማየት ማሰብ መሣል፣ የማይነጣሉ የሶስት ማዕዘናት ግንኙነት ያላቸዉ መሆናቸዉንም ይገልጻሉ። ከመምህሩ
ደቀ-መዝሙሩ እንዲሊ ተማሪዉ ከትምህርቱ በኋላ ከመምህሩ አንሶ ከተገኘ መምህሩ ተጠያቂ መሆኑን ተማሪዉ ከመምህሩ እኩል ሆኖ ከተገኘ ሁለቱም ተጠያቂ መሆናቸዉን፣ ተማሪዉ ከመምህሩ በልጦ ከተገኘ መምህሩ ተመስጋኝ መሆኑን የሚገልጹት ሰአሊ እሸቱ ጥሩነህ ኢትዮጽያ ጥንታዊ የሥዕል ቱፊት እንዳላት በኢትዮጽያ የሚገኙ የተለያዩ ታሪካዊ ቦታዎችን ማየት ይቻላል። ሙሉዉን ቅንብር ያድምጡ

አዜብ ታደሰ

ሸዋዪ ለገሰ 

Audios and videos on the topic