ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
በርካታ ወሳኝ ተጨዋቾች ለአፍሪቃ ዋንጫ ካሜሩን ባቀኑበት በአሁኑ ወቅት በተከናወነው የእንግሊዝ ፕሬሚየር ሊግ ሊቨርፑል እና ማንቸስተር ሲቲ ድል ቀንቷቸዋል። በቡንደስሊጋው መሪው ባየርን ሙይንሽን እና ተከታዩ ቦሩስያ ዶርትሙንድ ተጋጣሚዎቻችን በድምር 9 ግቦች አንኮታኩተዋል። ኖቫክ ጄኮቪች በውድድሩ ሳይሳተፍ ከአውስትራሊያ ተባሯል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን እሁድ ጥር 1 ቀን፣ 2014 ዓ.ም ካሜሩን ውስጥ ከኬፕ ቬርዴ ጋር ባደረገው የመጀመሪያ ግጥሚያ አብዛኛውን ሰአት በ10 ተጨዋቾች ተጋጥሞ አንድ ለዜሮ ተሸንፏል። በጀርመን ቡንደስሊጋ በርካታ ተጨዋቾቹን በኮቪድ-19 የተነሳ ማሰለፍ ያልቻለው ባየርን ሙይንሽን ሽንፈት ገጥሞታል።
33ኛው የአፍሪቃ ዋንጫ የእግር ኳስ ላይ ዘንድሮ ተሳታፊ የኾነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በነገው ዕለት ከአዘጋጅ ሀገሯ ካሜሩን ጋር ሁለተኛ ግጥሚያውን ያከናውናል። ዋሊያዎቹ ነገ ከካሜሩን ጋር በሚያደርጉት ግጥሚያ ፍጥነት እና ጉልበት የታከለበት አጨዋወት ይጠብቃቸዋል ተብሎ ይገመታል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ትናንት ከካሜሩን ጋር ባደረገው ግጥሚያ ሁለተኛ ሽንፈቱን አስተናግዷል። በተለይ የመጀመሪያው አጋማሽ ላይ ድንቅ ጨዋታ ያሳዩት ዋሊያዎቹ በካሜሩን 4 ለ1 ነው የተሸነፉት። ሦስተኛ ጥሩ ቡድን ወደ ቀጣዩ ዙር የማለፍ ዕድል አለው። ዋሊያዎቹ ቀጣይ ግጥሚያቸው ከቡርኪና ፋሶ ጋር ነው።