ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን እሁድ ጥር 1 ቀን፣ 2014 ዓ.ም ካሜሩን ውስጥ ከኬፕ ቬርዴ ጋር ባደረገው የመጀመሪያ ግጥሚያ አብዛኛውን ሰአት በ10 ተጨዋቾች ተጋጥሞ አንድ ለዜሮ ተሸንፏል። በጀርመን ቡንደስሊጋ በርካታ ተጨዋቾቹን በኮቪድ-19 የተነሳ ማሰለፍ ያልቻለው ባየርን ሙይንሽን ሽንፈት ገጥሞታል።
33ኛውን የአፍሪቃ እግር ኳስ ዋንጫ ልዩ ብቃታቸውን ያስመሰከሩት ሴኔጋሎች ለመጀመሪያ ጊዜ በእጃቸው አስገብተዋል። በእንግሊዝ ፕሬሚየር ሊግ ለሊቨርፑል በአጥቂ መስመር የሚሰለፈው ሳዲዮ ማኔ ነበር የማሸነፊያዋን የመጨረሻ የመለያ ምት የመታው። ሌላኛው የሊቨርፑል አጥቂ ሞሐመድ ሳላኅ በእንባ ተውጦ አምሽቷል።
ለአፍሪቃ ዋንጫ ማጣሪያ ማዳጋስካር ከነገ በስትያ ዋሊያዎቹን ይገጥማል። በፕሬሚየር ሊጉ ዌስትሀም እና አርሰናል ተጋጥመው ነጥብ መጣላቸው ለሊቨርፑል በጅቶታል። በጀርመን ቡንደስሊጋ መሪው ባየር ሙይንሽን ገና በ12ኛው ደቂቃ አንድ ተጨዋቹ በቀይ ካርድ ከሜዳ ቢሰናበትበትም ሽቱትጋርትን 4 ለ0 አንኮታኩቷል።