ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ | ስፖርት | DW | 15.12.2008
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ስፖርት

ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ

...ከሁለት ዓመታት በፊት በሶስተኛ ዲቪዚዮን ይጫወት የነበረው ሆፈንሐይም ታላላቆቹን እነባየር ሙኒክን ልቆ አሁንም በአንደኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። የሚገርመው ነገር አቻ የመውጣቱ አባዜ ከእንግሊዝ ፕሬሚየር ሊግ ተሻግሮ ቡንደስሊጋም መግባቱም ነው።

ቡንደስሊጋ-ሆፈንሀይም ከሻልካ

ቡንደስሊጋ-ሆፈንሀይም ከሻልካ

በዛሬው የስፖር ዝግጅታችን፤ በአውሮጳ ምድር የተከናወኑ አበይት የእግር ኳስ ውድድሮች፣ አትሌቲክስና እዚህ ጀርመን ውስጥ በጉጉት ሲጠበቅ ቆይቶ ቅዳሜ ማታ የተደረገ ያለም ከባድ ሚዛን የቡጢ ፍልሚያ ሰፊ ቦታ ተሰጥቷቸው ይተነተናሉ። ዝነኛው የዓለም ከባድ ሚዛን ቡጢኛ ዩክሬናዊው ቭላድሚር ክሊችኮ ቅዳሜ ማታ አሜሪካዊው ሀሲም ራህማንን አብረከረከ። ክሊችኮ በግራ እጁ ደጋግሞ የሰነዘራቸውን ከባድ ቡጢዎች መቓቓም የተሳነው ራህማን በስድስተኛው ዙር ተዘርሮም ነበር። ዳኛው ጠጋ ብለው ሲጠይቁት ጨዋታውን መቀጠል መፈለጉን የገለፀው አሜሪካዊ ቡጢኛ ከቀጣዩ ሰባተኛ ዙር በላይ ግን መዝለቅ አልቻለም።