ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
የኦሮምያ ክልል መንግሥት በክልሉ ለሚደረገዉ የሰላም ጥረት ድጋፍ መጠየቁ፤ ስድስት ወራት የሞሉት የፕሪቶርያ ስምምነት አተገባበር ፍጥነት ይጎድለዋል መባሉ፤ ጉምቱዉ ፖለቲከኛ ልደቱ አያሌዉ ወደ ሃገር ቤት ሊመለሱ መሆኑ እንዲሁም በ 32 ቋንቋዎች የሚራጨዉ ዶቼ ቬለ 70ኛ ዓመቱን እያከበረ መሆኑ በተሰኙ ርዕሶች ስር የተሰጡ ርዕሶችን ጨምቀን ይዘናል።
ለሰላም ድርድሩ መሳካት እዉቅና የተሰጣቸዉ ሰዎች ጉዳይ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት «ኦነግ ሸኔ» ከሚለው እና ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ከሚለው ታጣቂ ቡድን ጋር የሚያደርገው የሰላም ድርድር ፣የክልል ርዕሰ መስተዳድሮች የመቀሌ ጉብኝት እንዲሁም የሱዳን ወቅታዊ ሁኔታ በዚህ ሳምንት በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ያነጋገሩ ጉዳዮች ናቸው።
ላለፉት አራት ዓመታት ገደማ ኢትዮጵያ ከአንዱ አለመረጋጋት ወደሌላው ስትሸጋገር ኅብረተሰቡም በስጋት ድባብ እንደተዋጠ ዘልቋል።
በዛሬው የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ቅኝት መሰናዶ፦ የሰሜን ሸዋው ጥቃት፤ የሲኖዶስ ሕገወጥ የጳጳሳት ሹመት የቀሰቀሰው ቁጣ እንዲሁም የአቶ በረከት ስምዖን መፈታት ላይ እናተኩራለን። አስተያየቶቻችሁ የተሰባሰበበትን ጥንቅር ሙሉ ዘገባ በድምፅ ማድመጥ ይቻላል።