ሠራዊቱ መቀሌን መቆጣጠሩና የሕዝብ ስሜት | ኢትዮጵያ | DW | 30.11.2020
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ሠራዊቱ መቀሌን መቆጣጠሩና የሕዝብ ስሜት

ባለፈው ቅዳሜ ኅዳር 19 ቀን 2013 ዓ ም አመሻሽ ላይ የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት የመቀሌ ከተማን መቆጣጠሩን መንግሥት ይፋ ካደረገ በኋላ ኅብረተሰቡ በተለያዩ መንገዶች ስሜት ድጋፉን ሲገልጽ ተስተውሏል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 02:49

«የሕዝብ አስተያየት»

ባለፈው ቅዳሜ ኅዳር 19 ቀን 2013 ዓ ም አመሻሽ ላይ የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት የመቀሌ ከተማን መቆጣጠሩን መንግሥት ይፋ ካደረገ በኋላ ኅብረተሰቡ በተለያዩ መንገዶች ስሜት ድጋፉን ሲገልጽ ተስተውሏል። በአማራ ክልል በተለያዩ ከተሞች ሕዝብ ደስታውን ጥይት ወደሰማይ በመተኮስ፣ ሕጻናት ሳይቀሩ በመጨፈርና የመኪና ጥሩንባ በማሰማት በየከተሞቹ በመዞር ደስታውን መግለጹ ተሰምቷል።  በቆቦ ከተማ ደግሞ ትናንት እሁድ ጠዋት ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ መካሄዱን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ከየከተሞቹ የአንዳንዶቹን አስተያየተቶች አሰባስበናል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በዕለቱ በነበረው ሁኔታ በጥንቃቄ ጉድለት በተተኮሱ ጥይቶች ሕይወት መጥፋቱን አስተያየት ሰጪዎች ተናግረዋል። የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር መሠረት ደባልቄ በባሕር ዳር ከተማ አንድ ወጣት በዚሁ ጥንቃቄ በጎደለው መልኩ በተተኮሰ ጥይት መገደሉን ለዶይቼ ቬለ አረጋግጠዋል። ኅብረተሰቡ ተመሳሳይ ደስታዎች ሲያጋጥሙት ስሜቱን በአግባቡና በጥንቃቄ መግለፅ እንዳለበትም ፖሊስ አሳስቧል።

ዓለምነው መኮንን

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች