ሠላማዊ ሰልፍና ተቃዋሚ ፓርቲዎች በኢትዮጵያ | ኢትዮጵያ | DW | 29.09.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ሠላማዊ ሰልፍና ተቃዋሚ ፓርቲዎች በኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ ኅብረ-ብሔራዊና በብሔር ላይ የተመሰረቱ የተለያዩ ፓርቲዎች ካለፉት 22 ዓመታት አንስቶ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛሉ። ፓርቲዎች ሕገመንግሥቱን አክብረው በሠላማዊ መንገድ መንቀሳቀስ እንደሚችሉ በሕገመንግሥቱ ተቀምጧል። ሆኖም ከ1997ቱ ምርጫ ወዲህ በሠላማዊ መንገድ የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ማነቆዎች እንደበዙባቸው በተደጋጋሚ ሲገልፁ ይደመጣል።

ለአብነት ያህል ፓርቲዎች የተለያዩ ሕዝባዊ ስብሰባዎችንና የተቃውሞ ሠልፎችን ስንጠራ ያጋጥሙናል ያሉትን ችግሮች እንደማነቆ ያነሳሉ። የዛሬው የውይይት መድረክ ዝግጅታችንም ርዕስ «ሠላማዊ ሰልፍ እና ተቃዋሚ ፓርቲዎች በኢትዮጵያ» ይሰኛል። ለውይይቱ ሶስት እንግዶችን ጋብዘናል። ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት የሠማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ናቸው። አቶ ዳንኤል ተፈራ፤ በአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትኅ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ። እንዲሁም አቶ ያሬድ ኃ/ማርያም የኢትዮጵያ ሠብዓዊ መብቶች ጉባኤ የቀድሞ የምርመራ ሠራተኛ፤ በአሁኑ ወቅት በቤልጂየም ብራስልስ የሕግ ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ የሚገኙ የሠብዓዊ መብት ተሟጋች ናቸው። አቶ ያሬድ። እንግዶቻችን ለውይይቱ ፈቃደኞች በመሆናችሁ በአድማጮች ስም ከልብ አመሠግናለሁ። በመጀመሪያ ደረጃ አድማጮች ለውይይቱ የያዝነው ጊዜና ቦታ ስለማይፈቅድልን በርካታ ፓርቲዎችን ማሳተፍ አልቻልንም። ሁለቱን ፓርቲዎች ስንጋብዝም ያለምንም መስፈርት እንደሆነ ከወዲሁ እንድትገነዘቡልን እንፈልጋልን። ከመንግሥት በኩል በስብሰባ እና በተለያዩ ምክንያቶች ለውይይቱ የሚሳተፍ ሰው ማግኘት አልቻልንም።

ሙሉ ውይይቱን ከታኝ የሚገኘውን የድምፅ መጫወቻ በመጫን ያዳምጡ።

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ልደት አበበ

Audios and videos on the topic