ሠላማዊ ሰልፉ ታገደ | ኢትዮጵያ | DW | 01.05.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ሠላማዊ ሰልፉ ታገደ

ከአስተባባሪዎች አንዱ የሆኑት መምህር ክብሩ ማሞ መንግስት ዜጎችን ያፈናቀሉ ግለሰቦችና ቡድኖችን በሕግ ለመጠየቀ ቃል ከመግባት የዘለለ ተግባራዊ ርምጃ እንዲወስድ የሚጠይቁ መልዕክቶችን ለማስተጋባት ታስቦ አንደነበር ገልጸዋል። 

አውዲዮውን ያዳምጡ። 02:48

ሠልፉ ታገደ

ከደቡብ ኢትዮጵያ ከወደ ዲላ የደረሰን ዘገባም መንግሥት የጎሳ ግጭት፣ ግድያና መፈናቀለን እንዲያስቆም የአካባቢዉ ነዋሪዎች መጠየቃቸዉን የሚጠቁም ነዉ። ኢትዮጵያ ዉስጥ ባለፈዉ አንድ ዓመት በጎሳ ላይ ባነጣጠሩ ጥቃቶች በርካታ ሰዉ ከተገደለና ከተፈናቀለባቸዉ አካባቢዎች አንዱ የጌድኦ ዞን ነዉ።ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የሚሆን ሕዝብ ተፈናቅሏል።መንግስት ለተፋናቃዮቹ ድጋፍ እንዲያደርግ እና አፈናቃዮችን ለፍርድ እንዲያቀርብ ተበዳዮችና ለተበዳዮች የሚቆረቆሩ ወገኞች ባደባባይ ሠልፍ ለመጠየቅ ተዘጋጅተዉ ነበር።ዲላ ዉስጥ ይደረጋል ተብሎ የነበረዉ ሠልፍ አደራጆች እንደሚሉት የአካባቢዉ ባለሥልጣናት ሠልፉን ከፈቀዱ በኋላ ትናንት ማታ አግድዉታል።
የሰለፉ አስተባባሪዎች እንዳሉት ዛሬ ሊያካሂዱት የነበረው ሰልፍ ዋንኛ ዓላማ መንግስት በማንነት ላይ ባተኮሩ ጥቃቶችና መፍናቀሎች እየተዳረገ ለሚገኘው የጊዲኦ ህዝብ ተገቢውን ትኩረት እንዲሰጥ ለማሳሳብ የታለመ ነበር።ተፍናቃዮቹን ወደ ቦታቸው በመመለስ ዳግም እንዲያቂቂሙ መጠየቅና ደራሽ ዕረዳታዎችን እየለገሱ ለሚገኙ አካላት ምስጋና ማቅረብ ሌላው የሰልፉ ትኩረት ነበርም ብለዋል።ሰልፉን ያገዱት ባለስልጣናትን የሐዋሳዉ ወኪላችን ለማነጋገር ሞክሮ ነበር።ነገር ግን ባለስልጣናቱ ግምገማ ላይ ናቸዉ» የሚል መልስ ነዉ ያገኘዉ። 

በተለይም ከአስተባባሪዎች አንዱ የሆኑት መምህር ክብሩ ማሞ መንግስት ዜጎችን ያፈናቀሉ ግለሰቦችና ቡድኖችን በህግ ለመጠየቀ ቃል ከመግባት የዘለለ ተግባራዊ እርምጃ እንዲወስድ የሚጠይቁ መልዕክቶችን ለማስተጋባት ታስቦ አንደነበር ገልደዋል። 

ሰላማዊ ሰልፍን በዛሬው ዕለት ለማካሄድ ከዲላ ከተማና ከጊዲኦ ዞን አስተዳደር ፍቃድ ማግኘታቸውን የጠቀሱት የዝግጅቱ አስተባባሪ ሰልፉን ፍዱም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ለማከናወን መልዕክቶችን ያዘሉ ከኔቴራዎችና መፈክሮች ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል። 
ይሁንእንጂ ህገ መንግስታዊ መብቱን ተጠቅሞ ጥያቂውን ለማቅረብ በተዘጋጀበትና በርቀት የሚገኙ የሰለፉ ተሳታፊዎች ምሽቱን ወደ ዲላ ከተማ እየገቡ ባሉበት ወቅት ሰልፉ ማካሄድ እንደማይችሉ የሚገለድ ደብዳቤ እንደደረሳቸው አስተባባሪው ገልደዋል። 

አስተባባሪዎቹ በዚሁ መግለጫው ጋዜጠኞች እንዲያነቡት በማስረጃነት ያቀረቡትና ከዲላ ከተማ አስተዳደር ድህፈት ቤት ተልኪል በተባለው ደብዳቤ ላይ የፀጥታ ችግር መኖሩ ከፊደራልና ከክልል በተነገረን መሰረት ሰልፉ ለሌላ ጊዜ መዛወሩን እንገልፃለን በሚል አጭር አርፍተ ነገር መዳፉን ለመመልከት ችያልሁ። መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ከተያዘው ዓመት መግቢያ አንስቶ ከምስራቅና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች የተፈናቀሉ ከግማሽ ሚሊዮን የበላይ የጊዲኦ ተወላጆች በተለያዩ የስደተኛ ካምቦች ኑራቸውን በአስችጋሪ ሁኔታ እየገፉ ይገኛሉ።

ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ

ነጋሽ መሐመድ

እሸቴ በቀለ

Audios and videos on the topic