ሞባይል፣ የአፍሪቃ የመገናኛ ጸጋ፣ | ሳይንስ እና ኅብረተሰብ | DW | 23.09.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ሳይንስ እና ኅብረተሰብ

ሞባይል፣ የአፍሪቃ የመገናኛ ጸጋ፣

በተፈጥሮ ሀብት የታደለው ሆኖም፣ በኢንዱስትሪ መስፋፋት ረገድም ሆነ በመሠረተ ልማት ወደ ኋላ የቀረው የአፍሪቃው ክፍለ ዓለም፣ ዕድገቱን ለማፋጣን ከሚበጁት ዋና - ዋና ጉዳዮች አንዱ ፣ የስልክና የኢንተርኔት መረብ መሆኑ የሚታበል አይደለም።

default

አፍሪቃዊ፣ የሞባይል ተጠቃሚ፣

የኢንተርኔቱ መረብ እንደሚፈለገው ሊዘረጋ ባይችልም ሌላው ፈጣን የመገናኝ መሣሪያ ፣ ማለትም የእጅ ስልክ ( «ሞባይል»)ባልታሰበ ፍጥነት መስፋፋቱ አስገርሟል። እ ጎ አ ከ 2000 ዓ ም ወዲህ በሞባይል የሚጠቀሙት አፍሪቃውያን ቁጥር፣ ከ 20 ሚልዮን ወደ 400 ሚልዮን ከፍ ባሏል። የቋሚ ስልክ አገልግሎት እስከዚህም ሊስፋፋ አልቻለም ። እምብዛም ተፋላጊም ሆኖም አልታየም። በመሆኑም፣ የአፍሪቃ ባንኮችና የኢንተርኔት መረብ ኩባንያዎች፣ የእጅ ስልክ ተጨማሪ አገልግሎቶች መስጠት እንደሚችል በመገንዘብ፣ ለዚህ የመገናኛ ዘዴ ልዩ ትኩረት ሰጥተዋል። ምዕራቡ ዓለምም በአድናቆት በመመልከት ላይ ነው ተብሏል።

በደቡብ አፍሪቃ፣ ከየ10ሩ የአገሪቱ ኑዋሪ 9ኙ የአጅ ስልክ፣ ከየ 10 ሩ አንዱ ደግሞ የኢንተርኔት መስመር አለው። ሰለዚህ ባንኮች፣ በሞባይል ፣ ገንዘብ ማስተላለፍና የተቀማጭ ገንዘብን አያያዝ መምራት እንደሚቻል ለደንበኞቻቸው በማስረዳት አየተጠቀሙበት ነው።

ተክሌ የኋላ፣ ሸዋዬ ለገሠ

ተዛማጅ ዘገባዎች