1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሞሮኮ እና የተሀድሶ ለውጡ ንቅናቄ

ቅዳሜ፣ ሰኔ 4 2003

በሊቢያ፡ በየመን እና በሶርያ የቀጠለው ውዝግብ እና የህዝብ ዓመጽ በሰሜን አፍሪቃዊቱ ሀገር ሞሮኮ የሚካሄደውን የተቃውሞ ንቅናቄ ከዓለም መገናኛ ብዙኃን ትኩረት እንዲርቅ አድርጓል።

https://p.dw.com/p/RT7V
የተቃውሞ ንቅናቄ በሞሮኮምስል AP

ይሁንና፡ በዘውድ አስተዳደር በምትመራዋ የሰሜን አፍሪቃዊቱ ሀገር ሞሮኮም ውስጥ በሺዎች የሚቆጠሩ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲስፋፋ በመጠየቅ አደባባይ መውጣታቸውን እና የሀገሪቱ ፖሊስም በተቃዋሚ ሰልፈኞች አንጻር በኃይሉ ተግባር መጠቀሙን እንደቀጠለ ይገኛል። በሞሮኮ የተሀድሶ ለውጡ ንቅናቄ የጀመረው ትግሉ የተሳካ ውጤት ያስገኝለት አያስገኝለት በቅርብ ቀናት ውስጥ ይለያል ተብሎ ይጠበቃል።

ማርክ ዱገ

አርያም ተክሌ