ሞሮኮ በ2.3 ቢሊዮን ዶላር በድሬዳዋ ፋብሪካ ልትገነባ ነው | ኢትዮጵያ | DW | 19.11.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ሞሮኮ በ2.3 ቢሊዮን ዶላር በድሬዳዋ ፋብሪካ ልትገነባ ነው

ሞሮኮ የማዳበሪያ ማምረቻ ድሬዳዋ ከተማ ውስጥ በ2,3 ቢሊዮን ዶላር ለመገንባት ከኢትዮጵያ ጋር ስምምነት ተፈራረመች።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:00
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
04:00 ደቂቃ

ሞሮኮ በ2,3 ቢሊዮን ዶላር ድሬዳዋ ውስጥ የማዳበሪያ ፋብሪካ ልትገነባ ነው

የዓለም ግዙፉ የፎስፌት ማዕድን ላኪ የሞሮኮ ኩባንያ (OCP) የማዳበሪያ ማምረቻ ኢትዮጵያ ውስጥ በ2,3 ቢሊዮን ዶላር ለመገንባት ከኢትዮጵያ ጋር ስምምነት ተፈራረመ። በኢትዮጵያ በኩል ስምምነቱን የፈረመው በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን መኾኑም ተገልጧል። የማዳበሪያ ማምረቻ ፋብሪካው የሚገነባው ድሬዳዋ ከተማ ውስጥ እንደሆነም ተዘግቧል። ሞሮኮ ዘርፈ-ብዙ በኾኑ የትብብር መስኮች የተለያዩ ውሎችን ከኢትዮጵያ ጋር መፈራረሟን የአዲስ አበባው ወኪላችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ የላከው ዘገባ ይጠቁማል። የሞሮኮ ንጉሥ 6ኛው በኢትዮጵያ ያደረጉትን የ2 ቀናት ጉብኝት አጠናቀዋል።

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

እሸቴ በቀለ

Audios and videos on the topic