ምክር ቤታዊ ምርጫ በኒዠር | ኢትዮጵያ | DW | 20.10.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ምክር ቤታዊ ምርጫ በኒዠር

ኒዠር ውስጥ በዛሬው ዕለት ምክር ቤታዊ ምርጫ እየተካሄደ ነው።

default

ፕሬዚደንት ማማዱ ታንዣ

ድምጹን ለመስጠት የወጣው ህዝብ ቁጥር ያን ያህል ከፍተኛ አለመሆኑን የዜና ምንጮች ዘገባዎች አስታውቀዋል። የተቃውሞው ወገን ምርጫው ፕሬዚደንት ማማዱ ታንዣን ህገ መንግስቱ ከሚፈቅውደው የአስር ዓመት የስልጣን ዘመን በላይ ለማቆየት የታለመ ነው በሚል ህዝቡ ከድምጽ አሰጣጡ ስርዓት እንዲርቅ ቀደም ሲል ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል። የኒዠር ፕሬዚደንት ምርጫው ወደሌላ ጊዜ እንዲተላለፍ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በተደጋጋሚ ያሰማውን ጥሪ ችላ በማለታቸው በምህጻሩ ኤኮዋስ የምዕራብ አፍሪቃ መንግስታት የኤኮኖሚ ማህበር ሀገሪቱን ከድርጅቱ ለጊዜው አግልሎዋል።

ጌታቸው ተድላ/አርያም ተክሌ/ሸዋዜ ለገሰ

Audios and videos on the topic