ምናባዊ እውነታ በኢትዮጵያ | ኢትዮጵያ | DW | 04.02.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ምናባዊ እውነታ በኢትዮጵያ

አዲስ አበባ ተቀምጦ እንዴት ላሊበላን መጎብኘት ይቻላል? ወደ ናይሮቢ ኬንያ ሳይጓዙ፣ ወደ ዳካር ሴንጋል ወይም አክራ ጋና ሳይበሩ አዲስ አበባ ላይ ቁጭ ብሎ እንዴት ምሥጢራዊ ጎናቸዉን ማየት ይቻላል?

አውዲዮውን ያዳምጡ። 09:22

ምናባዊ እውነታ በኢትዮጵያ

የ iceaddis /አይስ-አዲስ/ የተሰኘዉ ጀማሪ የቴክኖሎጂ ድርጅት መሥራችና ሥራ አስኪያጅ የአቶ ማርቆስ ለማ ለዚህ ሁሉ ጥያቄ መልሱ Virtual Reality ወይም ምናባዊ እውነታ ነዉ ይላሉ። አቶ ማርቆስ የሚመሩት የቴክኖሎጂ ኩባንያዉ በአዲስ አበባ የሚገኘዉ የጎይቴ ተቋም ጋር በመተባበር ከጥር 14-19 ቀን 2010 ዓ/ም NEW DIMENSIONS Virtual Reality Africa በሚል ርዕስ በአዲስ አበበ ኤግዚቢሽን አዘጋጅቷል። አዘጋጆቹም ሰዎች ስለ ምናባዊ እውነታ ወይም Virtual Reality በደንብ እንዲረዱና አፍሪቃ ዉስጥ የተሰሩትን ፊልሞች እንዲመለከቱ ግብዣ አድርገዋል።

በዚህ ኤግዚቢሽን ወደ 2000 ሰዉ ይታደማሉ ተብሎ እንደተጠበቀ የሚናገሩት የአይስ-አዲስ መስራቹ አቶ ማርቆስ ከ7-10 ደቂቃ ርዝመት ያሏቸው አራት ፊልሞችን በአንድ ክፍል ዉስጥ ለሰባት ሰዉ እንዳሳዩ ይገልጻሉ።

ምናባዊ እውነታ ወይም Virtual Reality እየተስፋፋ ያለዉ የቴክኖሎጂ ውጤት ሲሆን የዚህን ቁሳቁስ በማምረት ኦኩላስ በቀዳሚነት ቢጠቀስም እነ ሶኒ፣ ሳምሶንግና ጉግል ኩባኒያዎችም ይገኙበታል። በኤግዚቢሽኑ ላይ ከታደሙት ዉስጥ አንዱ በቴክኖሎጂ ኢንጅኔሪንግ ሙያ ዉስጥ ያለው ተመስገን ፍሰሐ ይባላል።

ሌላዋ የኤግዚቢሽኑ ታዳሚ «በአይስ አዲስ» ረዳት አስተዳዳሪ ሕሊና ተስፋዬ ናት። የምናባዊ እውነታ ወይም Virtual Reality መነጽር በማድረግ በተቀመጠችበት ክፍል ውስጥ 360 ዲግሪ በመሽከርከር  ከ7 እስከ 10 ደቅቃ የሚወስድ ፊልም ማየት መቿሏ በጣም እንዳስገረማት ትናገራለች። በኤግዚቢሽኑ ላይ ለዕይታ ከቀረቡት ይሄን ያህል የሚያስፈራ ተንቀሳቃሽ ምስል እንደሌለ አቶ ማርቆስ ይናገራሉ።የምናባዊ እውነታ ወይም የVirtual Reality አሉታዊ ተጽእኖ እንዳለዉ ሁሉ አዎንታዊ ዉጤቶችም እንደሚኖሩትም አቶ ማርቆስ ሳይጠቅሱ አላለፉም። ለዚህም በምሳሌነት የጠቀሱት ይህን የሚያዘወትሩ በቀላሉ ሱሰኛ የሚሆኑበት ዕድል መኖሩን ነዉ።

እንደነዚህ ያሉ ቀን በቀን እያደጉ እና እየተስፋፉ የመጡት የቴክኖሎጂ ዉጤቶች የዓይን ቅንድብን በአስገርሞት የሚያስነሱ ናቸዉ። በምናባዊ እውነታ ወይም Virtual Reality አንበሳን ጨምሮ የዱር አራዊትን መዳሰስ፣ ሂማላያ ተራራን መዉጣት ወይም ባሉት ስፖርታዊ ጨዋታዎች መሳተፍ፣ ሌላም ሌላም ነገሮችን ማድረግ የሚያስችሉ ናቸዉ። እርሶ ይህን መሞከር ይፈልጋሉ? መልሱን ለእርስዎ ልተዉ።

መርጋ ዮናስ

ሸዋዬ ለገሰ

Audios and videos on the topic