ምስራቅ አፍሪቃን የመታዉ አስከፊ ድርቅ | ኢትዮጵያ | DW | 11.07.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ምስራቅ አፍሪቃን የመታዉ አስከፊ ድርቅ

የምስራቅ አፍሪቃ አገራትን ዘንድሮ የመታዉ እጅግ አስከፊ ድርቅ በከፋ ደረጃ ላይ ደርሶአል፣ በእንስሳት ሃብት ላይም ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል ሲሉ የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ እርዳታ ሃላፊ አስታወቁ።

default

ቫለሪ አሞስ

በምስራቅ ኢትዮጽያ የኦጋዴን አካባቢዎችን ተዘዋዉረዉ የጎበኙት የመንግስታቱ ማህበር የሰብአዊ ጉዳይ ምክትል ዋና ፀሐፊ ቫለሪ አሞስ ባዪት ነገር ሁሉ መደንገጣቸዉንና ማዘናቸዉን ገልጸዋል። እናቶች እና ህጻናት በከፍተኛ ደረጃ በምግብ እጥረት ተጠቅተዋል። ከፍተኛ የዉሃ እጥረት በመፈጠሩ ችግሩ በጥቂት ቀናት ዉስጥ ሊያከፋዉ ይችላል ሲሉ መግለጻቸዉን የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ታደሰ እንግዳዉ ከአዲስ አበባ የላከልን ዘገባ ያሳያል።

ታደሰ እንግዳዉ

አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሃመድ

Audios and videos on the topic