ምርጫ 2002-የድምፅ አሰጣጡ፦ ተስፋ፦ ዉዝግብና ወቀሳ | ኢትዮጵያ | DW | 23.05.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ምርጫ 2002-የድምፅ አሰጣጡ፦ ተስፋ፦ ዉዝግብና ወቀሳ

ኢትዮጵያዉያን በረዥም ጊዜ የነፃነት ታሪካቸዉ፥ በጥንታዊ ሥልጣኔያቸዉ፥ ሥር በሰደደ የመቻቻል ባሕላቸዉ የመታወቅ-የመኩራታቸዉን ያሕል፥ በድሕነታቸዉ ከመሳቀቅ፥ በሰላም እጦት ከመሞት፥ መንገላታት፥ መዋከብ የተለቃቀቁበት ዘመን ከነበረ-በጣም ጥቂት ነዉ።በተለይ በራሳቸዉ ድምፅ መሪያቸዉን ለመምረጥ-የሞከሩበት እንጂ የሹሙበት ዘመን የለም

default

ግንቦት 15 2002 ኢትዮጵያዉያን የወደፊት እንደራሴዎቻቸዉን ለመምረጥ ዛሬ ድምፅ ሲሰጡ ነዉ-የዋሉት።በታሪክ ለበለፀጉት ለኢትዮጵያና ኢትዮጵያዉያን ሌላ ታሪካዊ ዕለት ነዉ።የድምፅ አሰጣቱ ሒደት፥ የመራጩ ሕዝብ ስሜት፥የፖለቲከኞች ቅሬታና ወቀሳ፥ የታዛቢዎች ምሥክርነት፥ የአስመራጭ ኮሚሽን አስተያየት የልዩ ዝግጅታችን ትኩረት ነ

Wahlkampf Äthiopien 2010

ዉ።

ኢትዮጵያዉያን በረዥም ጊዜ የነፃነት ታሪካቸዉ፥ በጥንታዊ ሥልጣኔያቸዉ፥ ሥር በሰደደ የመቻቻል ባሕላቸዉ የመታወቅ-የመኩራታቸዉን ያሕል፥ በድሕነታቸዉ ከመንሳቀቅ፥ በሰላም እጦት ከመሞት፥ መንገላታት፥ መዋከብ የተለቃቀቁበት ዘመን ከነበረ-በጣም ጥቂት ነዉ።በተለይ በራሳቸዉ ድምፅ መሪያቸዉን ለመምረጥ-የሞከሩበት እንጂ የሹሙበት ዘመን የለም።የምዕራቡ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት በአብዛኛዉ አለም በተንሠራፋበት በቅርቡ ዘመን ኢትዮጵያዉያንም መሪዎቻቸዉን ለመምረጥ ሞክረዉ ነበር።ከዚሕ ቀደም ከተደረጉት ሰወስት ሙከራዎች በአንፃራዊ መመዘኛ የተሸለዉ የ1997ቱ ምርጫ ነበር።ዉጤቱና መዘዙ ግን የነበረዉን ተስፋ ሁሉ አጨናጎሎታል።

የ1997ቱ መርጫ-ዛሬ አምስት አመቱ።ዛሬም ምርጫ አለ።ወኪላችን ጌታቸዉ ተድላ የርዕሠ-ከተማ አዲስ አበባን አንዳድ የምርጫ ጣቢያዎች ተመልኳቷል።የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ቅሬታና ወቀሳ ግን እንደቀጠለ ነዉ።የመላዉ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ኢንጂነር ሐይሉ ሻዉል እንደሚሉት ገዢዉ ፓርቲ ኢሕአዴግ ሕግ ጥሶ የሚፈፀመዉ በደል በተለይ በአንዳድ ቦታዎች-ከሥሌት በላይ ነዉ።
ተንቤን-ትግራይ ዉስጥ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክን ወክለዉ የሚወዳደሩት የቀድሞዉ የመከላከያ ሚንስትር አቶ ስዬ አብረሐም ተመሳሳይ ቅሬታ አላቸዉ።

የተቃዋሚዎች ቅሬታና ወቀሳ ከሌሎችም አካባቢዎች እንቀጠለ ነዉ።ወቀሳና ቅሬታዉን በተመለከተ መልስ እንዲሰጡን የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሕዝብ ግንኙነት ሐላፊ አቶ መሐመድ አብዱረሕማንን ጋብዘናቸዋል። አቶ መሐመድን ነጋሽ መሐመስ አነጋግሯቸዋል።
የድምፅ አሰጣጡን ከሚከታተሉት መካከል የአዉሮጳ ሕብረት የታዛቢዎች ቡድን አንዱ ነዉ።የአንድ መቶ ሰባ አባላት ያሉት ቡድን መሪ ቲስ ቤርማንን አርያም ተክሌ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት በስልክ አነጋግራቸዉ ነበር።በዛሬዉ ምርጫ ከሰላሳ ሁለት ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ድምፅ ይሰጣል-ወይም እየሰጠ ነዉ። ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ብቻ ከሰባት ሺሕ በላይ እጩዎች ይፎካከራሉ።ከፍተኛ ፉክክር ከሚደረግባቸዉ አካባቢዎች አንዱን ሰሜን-ምዕራብ ኢትዮጵያን ወኪላችን ታደሰ እንግዳዉ ካለፈዉ አርብ ጀምሮ እየተዘዋወረ ነዉ።አርያም ተክሌ

Wahlplakate vor der Parlamentswahl in Äthiopien am 23.Mai

አነጋግራዋለች።

ዛሬ ጠዋት የአዲስ አባባዉን ሒደት የተከታተለዉ ጌታቸዉ ተድላ በአዲስ አባና በናዝሬት መሐል የሚገኙትን ከተሞች እየቃኘ ናዝሬት ደርሶ ሒደቱን ተመልክቷል። መሳይ መኮንን-ወደ መቀሌ፥ አዋሳ እና አርባ ምንጭ ሥልክ ደዉሎ ነበር።የመራጩ ሕዝብ ስሜትን በጥቂቱ፥-የነገሩት አሉ።ከምሥራቅ ኢትዮጵያ ዩሐንስን ገብረ እግዚ አብሔር ሐረር ላይ እየጠበቀን ነዉ።

ወኪሎች

አዜብ ታደስ

አርያም ተክሌ

መሳይ መኮንን

ሒሩት መለስ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic