ምርጫ 2002 የመጨረሻዉ ምዕራፍ | ኢትዮጵያ | DW | 27.05.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ምርጫ 2002 የመጨረሻዉ ምዕራፍ

በኢትዮጽያ በመጭዉ እሁድ የሚካሄደዉ 4ኛዉ አገር አቀፍ ምርጫ በመጨረሻዉ ሰአትም ዉዝግቦች አልተለለዩም። የሲዳማ አርነት ንቅናቄ፦ «በደቡብ ክልል በአሮሪሳ ወረዳ የድምጽ መስጪያ ወረቀት በገዝዉ ፓርቲ አማካኝነት በሚስጢር እየታደለ ነዉ»

default

በኢትዮጽያ በመጭዉ እሁድ የሚካሄደዉ 4ኛዉ አገር አቀፍ ምርጫ በመጨረሻዉ ሰአትም ዉዝግቦች አልተለለዩም። የሲዳማ አርነት ንቅናቄ፦ «በደቡብ ክልል በአሮሪሳ ወረዳ የድምጽ መስጪያ ወረቀት በገዝዉ ፓርቲ አማካኝነት በሚስጢር እየታደለ ነዉ» ይላል፣ የመላዉ ኢትዮጽያ አንድነት ፓርቲም ተመሳሳይ ክስ ያቀርባል። የደቡብ ክልል ፕሪዝደንት አቶ ሽፈራዉ ሽጉጤ በሚወዳደሩበት የአሮሪሳ ወረዳ ተከሰተ የተባለዉን የድምጽ መስጪያ ወረቀት በሚስጥር መበተንን በተመለከተ የክልሉ ምርጫ ቦርድ እያጣራ መሆኑን ገልጾአል። መሳይ መኮንን ሠወስቱን ወገኖች አንጋግሯቸዋል።

Wahlplakate vor der Parlamentswahl in Äthiopien am 23.Mai

ወደ ሰሜን ምዕራብ ኢትዮጽያ ስናቀና ደግሞ ወደ ባህር ዳር የተጓዘዉ ወኪላችን ታደሰ እንግዳዉ የምርጫዉ ዝግጅት መጠናቀቁን ገልጾአል። ይሁን እና እዝያም ቢሆን ተቃዋሚ ፓርቲዎች ቅሪታ ማሰማታቸዉ አልቀረም። ታደሰ እንግዳዉን ነጋሽ መሃመድ ስልክ ደዉሎ አግኝቶታል።

ተቃዋሚ ፓርቲዎች ገዥዉን ፓርቲ ኢሃኤግን ከመዉቀሳቸዉ ጋር አለማቀፉ ማህበረሰብ ኢትዮጽያ ዉስጥ የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታት ብዙም አልጣረም በማለት ቅሪታቸዉን እያሰሙ ነዉ። 8 የፖለቲካ ፓርቲዎችን የሚያጣምረዉ የኢትዮጽያ ፊደራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ሊቀመንበር ፕሮፊሰር በየነ ጴጥሮስ ትናንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ይህንኑ ቅሪታቸዉን በግልጽ አስታዉቀዋል። ፕሮፊሰር በየነ ጴጥሮስ የኢትዮጽያ መንግት መድረክን ግጭት ለመጫር እየተንቀሳቀሰ ነዉ ያለዉን ክስም አጣጥለዉታል። ሉድገር ሻዶምስኪ ከአዲስ አበባ የላከዉን የፕሮፊሰሩን መግለጫ መሳይ

Professor Beyene Petros derzeitiger Vorsitzender des Oppositionsbündnisses Medrek

ፕሮፊሰር በየነ ጴጥሮስ

መኮንን አዘጋጅቶታል።

ምሥራቅ ኢትዮጵያም የምርጫዉ ዝግጅት ተጠናቅቆ-መራጭና ተወዳዳሪዎች የድምፅ መስጪያዉን ዕለት እየተጠባበቁ ነዉ።የድሬዳዋዉ ወኪላችን ዩሐንስ ገብረ እግዚ አብሄር እንደተከታተለዉ የአዉሮጳ ሕብረት የምርጫ ታዛቢዎች ቡድን መሪ ቲስ ቤርማን ዛሬ ድሬዳዋ ዉስጥ የሚወዳደሩ ዕጩዎችን ፦ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችንና የምርጫ ቦርድ ተጠሪዎችን አነጋግረዋል።ነጋሽ መሐመድ ዩሐንስ ገ/እግዚአብሔርን በስልክ አነጋግሮታል።

Thijs Bergman

ቤርማን

መሳይ መኮንን

ታደሰ እንግዳዉ

ዩሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች