ምርጫ ቦርድ እውቅና የነፈጋቸው የመኢአድና የአንድነት አመራሮች ሮሮ | ኢትዮጵያ | DW | 30.01.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ምርጫ ቦርድ እውቅና የነፈጋቸው የመኢአድና የአንድነት አመራሮች ሮሮ

የምርጫ ቦርድ ህጋዊ እውቅና የነፈገው የአንድነት ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ በበኩሉ ጉዳዩን በፍርድ ቤት እንደሚከታተል አስታውቋል ።

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ትናንት እውቅና የነፈጋቸው የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መኢአድና የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ አመራር አባላት የምርጫ ቦርድን ውሳኔ አሳፋሪና አሳዛኝ ሲሉ ነቀፉ ። የመኢአድ አመራር አባል ለዶቼቬለ በሰጡት አስተያየት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከመኢአድ ራሱን ላገለለው አካል ዕውቅና መስጠቱ ህጋዊ አግባብ የለውም ብለዋል ። እነዚሁ የአመራር አባላት ዛሬ ከየፅህፈት ቤታቸው በፖሊስ እንዲወጡ መደረጉን የአዲስ አበባው ወኪላችን ዘግቧል ። በዚህ ምክንያት አመራሮቹ ስለ ትናንቱ የምርጫ ቦርድ ውሳኔ ሊያካሂዱ ያቀዱት ስብሰባና ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰርዟል ። የአዲስ አበባው ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሄር ዝርዝሩን ልኮልናል ።የምርጫ ቦርድ ህጋዊ እውቅና የነፈገው የአንድነት ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ በበኩሉ ጉዳዩን በፍርድ ቤት እንደሚከታተል አስታውቋል ።ሥራ አስፈፃሚው ከዚህም በተጨማሪ ለእሁድ በተለያዩ አካባቢዎች ተጠርቶ የነበረው የተቃውሞ ሰልፍ እንደተሰረዝና የፓርቲው አመራሮች ሌላ ፓርቲ የማያቋቁሙ የሌላ ፓርቲ አባል እንደማይሆኑና በኢትዮጵያም የመድብለ ፓርቲ ስርዓት ያበቃለት መሆኑን አስታውቋል ።በሌላ በኩል የመኢአድ ፅህፈት ቤት ለ24 ሰዓት ክፍት እንዲሆን ፖሊስ እንዳዘዛቸው አቶ ተስፋዮ ለሪፖርተራችን ገልጸዋል ።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ኂሩት መለሰ

ነጋሽ መሀመድ

Audios and videos on the topic