ምርጫ በደቡብ አፍሪቃ | አፍሪቃ | DW | 03.08.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

ምርጫ በደቡብ አፍሪቃ

በደቡብ አፍሪቃ ዛሬ የአካባቢዎች እና የከተሞች አስተዳደሮች ምክር ቤታዊ ምርጫ ተካሂዶዋል። ምርጫው ሀገሪቱ ከውሁዳኑ ነጮች አገዛዝ ከተላቀቀች ወዲህ በስልጣን ላይ ባለው የአፍሪቃውያን ብሔረተኞች እንቅስቃሴ ፓርቲ፣ በምህፃሩ በ«ኤ ኤን ሲ» አኳያ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጠንካራ ፉክክር የታየበት መሆኑ ተገልጾዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:59

ደቡብ አፍሪቃ

የምርጫ ውጤት ትንበያዎች እንደሚጠቁሙት፣ «ኤ ኤን ሲ» በአንዳንድ ትላልቅ ከተሞች ይዞት የነበረውን አብላጫ ድምፅ ያጣል። ፉክክሩ በተለይ በጆሀንስበርግ፣ ፕሪቶርያ፣ ጠንካራ እንደሆነ ተገነግሮዋል። በመጀመሪያ ምርጫው እንዴት እየተካሄደ እንደሆን የጆሀንስበርግ ወኪላችን መላኩ አየለን ስቱድዮ ከመግባቴ በፊት በስልክ ጠይቄዋለሁ።

መላኩ አየለ
አርያም ተክሌ
ነጋሽ መሀመድ

Audios and videos on the topic