ምርጫ በናይጀሪያ | ኢትዮጵያ | DW | 02.04.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ምርጫ በናይጀሪያ

ናይጀሪያውያን ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ እስከሚቀጥለው ሚያዝያ ስምንት ድረስ አዲስ ብሄራዊ እና የክፍላተ ሀገር ምክር ቤታዊ ምጫ፡ እንዲሁም የክፍላተ ሀገር አስተዳዳሪዎች ምርጫ ያካሂዳሉ።

default

እአአ የፊታችን ሚያዝያ ዘጠኝ አዲስ ፕሬዚደንት ይመርጣሉ። ናይጀሪያ ውስጥ እአአ በ 1999ዓም ስርዓተ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንደገና ከተተከለ ወዲህ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ሲደረግ ያሁኑ ሶስተኛ ይሆናል። አስመራጩ ኮሚስዮን ባለፉት ሁለት ምርጫዎች አንጻር ያሁኑን ምርጫ ሂደት ትክክለኛ እና ግልጽ ለማድረግ አቅዶዋል። ሀቀኛው ስርዓተ ዴሞክራሲ ለናይጀሪያ የኤኮኖሚውን ዕድገት እንደሚያስገኝላት ዜጎችዋ ብቻ ሳይሆኑ የውጭው ዓለም ተስፋ አድርጎዋል።