ምርጫና እና ወጣቱ | ባህል | DW | 22.05.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

ምርጫና እና ወጣቱ

አምስተኛው የኢትዮጵያ አገር አቀፍ ምርጫ ሊካሄድ ሁለት ቀናት ቀርተውታል። ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ስለምርጫው ዘመቻ በአጠቃላይ ምን ይላሉ? የተወሰኑት ፤ የታዘቡትን አካፍለውናል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 09:48

ምርጫና ወጣቱ

ኢትዮጵያ ውስጥ በአሁኑ ወቅት ትልቁ ዜና የፊታችን ዕሁድ የሚካሄደው 5ኛው አጠቃላይ ምርጫ ነው። ለምርጫው በተለይ በሀገሪቱ ትላልቅ ከተሞች የምርጫው ቅስቀሳ ሰሞኑን ተጠናክሮ ሲካሄድ ሰንብቷል። ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ስለምርጫው ዘመቻ በአጠቃላይ ምን ይላሉ? የተወሰኑት ፤ የታዘቡትን አካፍለውናል።

ለምሳሌ ሰሜን ሸዋ የምትገኘው የአጣዬ ከተማ ነዋሪ ወጣት የምርጫው ዕለት የሚሰጠውም ድምፅ ተግባር ላይ መዋሉን አብዝቶ ይጠራጠራል። ሌላው ወጣት ምርጫ መኖሩን የሚያሳይ አንዳችም ምልክት አለመመልከቱን ገልፆልናል።

አንድ አዲስ አበባ ነዋሪ ወጣት ደግሞ ፤ እንደገለፀልን ምንም እንኳን የመምረጥ ዕድል ሲያገኝ ያሁኑ የመጀመሪያው ቢሆንም በምርጫው የመሳተፍ ፍላጎቱ ያን ያህል አይደለም። ሌላው በሚኖርበት አካባቢ የምርጫው ሳምንት ምን እንደሚመስል የገለፀልን ወጣት ፤ የባቢሌ ወረዳ ነዋሪ ነው። ወጣት መስፍን ደግሞ በቡታጅራ ማንኛውም የምርጫ ፓርቲዎች ቅስቀሳ ሲካሄድ አላየሁም ቢልም ዕሁድ የሚካሄደውን ምርጫ አስመልክቶ ፤ በአካባቢው በተደረገው ስብሰባ ላይ መገኘቱን ግን ገልፆልናል።

እሁድ ግንቦት 16 ቀን 2007 ዓ.ም የሚካሄደውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ሰሞን አስመልክቶ ፤ በተለያየ የሀገሪቱ ክፍል ከሚገኙ ጥቂት ወጣቶች በድምፅ የገለፁልንን እዚህ ጋ ያገኙታል።

ልደት አበበ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic