ምላዲች እና የዴን ኻጉ ፍርድ ቤት | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 30.05.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

ምላዲች እና የዴን ኻጉ ፍርድ ቤት

ዴን ኻግ ውስጥ ሲጠበቁ ብዙ ጊዜ አልፎዋል፡ የቀድሞው የቦዝንያ ሰርቢያውያን ዋና ጦር አዛዥ፡ ራትኮ ምላዲች።

default

ለምላዲች የድጋፍ ሰልፍ

ምላዲች በስሬብሬኒሳ እአአ በ1995ዓም ለተፈጸመው እና ስምንት ሺህ ሰዎች ለተገደሉበት ጭፍጨፋ በዩጎዝላቭያ ጦር ወንጀል ተመልካች ፍርድ ቤት ፊት ቀርበው መልስ እንዲሰጡ ቤልግሬድ የሚገኝ አንድ ፍርድ ቤት ሰሞኑን ወስኖዋል። የምላዲች ጠበቆች በዚሁ ውሳኔ አንጻር ይግባኝ ማመልከቻ ለማስገባት አስበዋል። በሰርቢያ ብዙ የምላዲች ደጋፊዎች በፍርድ ቤቱ ውሳኔ አንጻር ተቃውሞ በማሰማት ላይ ሲሆኑ፡ የዶይቸ ቬለ ባልደረባ ዮርግ ፓስ እንድሚለው፣ እነርሱ ምላዲችን እንደ ወንጀለኛ ሳይሆን እንደአርበኛ ነው የሚመለከቱዋቸው።

ዮርግ ፓስ
አርያም ተክሌ

ሸዋዬ ለገሰ

Audios and videos on the topic