ሜቄዶኒያ የአረጋውያንና ሕሙማን መርጃ ማዕከል | ኢትዮጵያ | DW | 17.03.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ሜቄዶኒያ የአረጋውያንና ሕሙማን መርጃ ማዕከል

ሜቄዶኒያ የአረጋውያን እና የአዕምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል የተሰኘው የበጎ አድራጎት ድርጅት አረጋውያንን እና የአዕምሮ ኅሙማንን በበጎ ፈቃደኝነት መርዳት እንደሚገባ አሳሰበ።

Gambia Street in Addis Abeba, Äthiopien

የማዕከሉ ሥራ አስኪያጅ አቶ ቢንያም በለጠ ይኽን ያሳሰቡት እሁድ በሚሊኒየም አዳራሽ የተኪያሄደውን የገቢ ማሰባሰቢያ እና የምሥጋና መርሃ-ግብር አስመልክቶ ለዶይቸ ቬለ በሰጡት አስተያየት ነው። በገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ-ግብሩ ዘጠኝ ሺህ ሰው መታደሙ ተገልጧል፤ የ15 ሚሊዮን ብር ዕርዳታ ከሕዝቡ ቃል ተገብቷል። አንድ መነኩሴ ልጃቸው ከውጪ ሀገር የላከላቸውን መኪና በርዳታ ለግሰዋል። ለማዕከሉ ሕንፃ የመጀመሪያ ደረጃ ግንባታ እስከ 300 ሺህ ብር እንደሚያስፈልግም ተጠቅሷል።

ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic