ሜሽካርት-የኢትዮጵያውያኑ ድረ-ገጽ መገበያያ | ባህል | DW | 08.01.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

ሜሽካርት-የኢትዮጵያውያኑ ድረ-ገጽ መገበያያ

በሁለት ወጣት ኢትዮጵያውያን የተመሠረተው ሜሽካርት ድረ-ገጽ መገበያያ፤ የኢትዮጵያ ቡና፣ ሽሮ፣ በርበሬ፤ አልባሳት፤ መጻሕፍት፤እና መጽሄት እንዲሁም በርካታ ቁሳቁሶች የሚሸጡበት ድረ-ገጽ ነው። ወጣቶቹ በአሜሪካን በተማሩበት ዘርፍ ሥራ ማግኘት ቀላል እንዳልሆነ ይናገራሉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 12:00
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
12:00 ደቂቃ

የሜሽካርት መስራቾቹ ኢትዮጵያውያን

አነስተኛ ዋጋ፣ ሰፊ ምርጫ፣ ፈጣን አቅርቦት ታዋቂው የድረገጽ የግብይት መድረክ አማዞን የሚታወቅበት መርኁ ነው። የዛሬ የወጣቶች ዓለም ትኩረታችን ግን ስለ አማዞን አይደለም። አሜሪካን ሀገር በሚኖሩ ሁለት ኢትዮጵያውያን ስለ ተመሰረተው ሜሽካርት የድረገጽ ገበያ እንጂ። ሽሮ፣ በርበሬ፣ አልባሣት፣ የሙዚቃ እና የፊልም ሲዲዎች ስለሚሸጡበት የድረገጽ ገበያ ነው የምናወሳው። ሜሽካት የድረገጽ ገበያ በአሜሪካን ከ25 ግዛቶች በየጊዜው ትዕዛዝ ይቀበላል። ግብይቱ በተፈጸመ በ2 ቀናት ውስጥ የገዢው መኖሪያ ድረስ ዕቃው እንደሚደርስ መሥራቾቹ ይናገራሉ። የዋሽንግተኑ ወኪላችን ናትናኤል ወልዴ ወጣቶቹን አነጋግሮ የሚከተለውን ዘገባ ልኮልናል።

ናትናኤል ወልዴ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic