ሜርክል ለ4ኛ የስልጣን ዘመን መወዳደር ይሻሉ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 21.11.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

ሜርክል ለ4ኛ የስልጣን ዘመን መወዳደር ይሻሉ

የጀርመኗ መራሂተ-መንግሥት አንጌላ ሜርክል በሚቀጥለው ዓመት በሚደረገው ምርጫ ለአራተኛ የስልጣን ዘመን እንደሚወዳደሩ ተናገሩ። አንጌላ ሜርክል ለወግ አጥባቂው ክርስቲያ ዴሞክራቶች ፓርቲ አባላት በሚቀጥለው ዓመት በሚካሔደው ምርጫ ለመወዳደር እንደሚፈልጉም ገልፀዋል።

 

 

ባለፉት ወራት መራሂተ መንግሥትዋ እንደሚወዳደሩ መናገራቸውን የውስጥ አዋቂ ምንጮችን ጠቅሶ ሲኤን ኤን የዜና አገልግሎት በሰፊዉ ዘግቦ ነበር።  ሜርክል በሚቀጥለው ወር በሚካሔደው የወግ አጥባቂው ክርስቲያን ዴሞክራቶች ፓርቲ ዓመታዊ ጉባዔ ላይ የ62 አመቷ አንጌላ ሜርክል ራሳቸውን በእጩነት እንደሚያቀርቡም ታዉቋል። የፊዚክስ ባለሙያዋ አንጌላ ሜርክል ወደ መራሒተ መንግሥትነት የመጡት በጎርጎሮሳዊው 2005 ዓ.ም. ሲሆን የመጀመሪያዋ የጀርመን ሴት መሪ ናቸው።

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ