ሜርክል ለአራተኛ ጊዜ መራሒተ መንግሥት ሆነዉ ተመረጡ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 14.03.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አውሮጳ/ጀርመን

ሜርክል ለአራተኛ ጊዜ መራሒተ መንግሥት ሆነዉ ተመረጡ

ላለፉት 12 ዓመታት በሥልጣን ላይ በመራሒ መንግሥትነት ያገለገሉት አንጌላ ሜርክል ለተጨማሪ አራት ዓመታት መሪ ሆኖ እንዲቀጥሉ በድጋሚ ተመረጡ። ወይዘሮ አንጌላ ሜርክል ከካቢኔ አባሎቻቸዉ ጋር ለሃገር ጥቅም፤ ህዝብ እና ለሃገር ደህንነት እስከ መጨረሻዉ ለመስራት በእግዚአንሄር ስም ቃል እገባለሁ ሲሉ ቃለ መሃላም ሰጥተዋል።

በጀርመን ተወካዮች ምክር ቤት አብላጫ መቀመጫ ያላቸው ሦስት ፓርቲዎች አዲስ ጥምር መንግሥት ለመመስረት የደረሱበትን ስምምነት በያዝነዉ ሳምንት መጀመርያ በፊርማ አጽቀዋል።፡፡ፓርቲዎቹ የተፈራረሙት ሥምምነት በሚቀጥሉት አራት ዓመታት ጀርመንን የሚመራው ጥምር መንግሥት የሚከተላቸውን ፖሊሲዎች የያዘ ነው።

የስምምነቱን መጽደቅ ተከትሎ የሀገሪቱ የተወካዮች ምክር ቤት አንጌላ ሜርክልን መራሂተ መንግሥት አድርጎ ዛሬ ረቡዕ ይሰየማል ተብሎ ተጠብቆ ነበር፡፡

 ጀርመናውያን ምርጫ ያካሄዱት ባለፈው መስከረም ወር ሲሆን በምክር ቤት መቀመጫ ያገኙ ፓርቲዎች መንግሥት መመስረት ባለመቻላቸው መራሂተ መንግሥት ሜርክል ሀገሪቱን በሞግዚትነት ሲያስተዳድሩ ቆይተዋል፡፡ መንግሥት ሳይመሰረት የተቆየበት የ171 ቀናት ጊዜ በጀርመን ታሪክ ረጅሙ ነው ተብሎለታል፡፡

አዜብ ታደሰ

ኂሩት መለሰ