ማዶና እና የማደጎዉ ግርግር | የጋዜጦች አምድ | DW | 23.10.2006
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

የጋዜጦች አምድ

ማዶና እና የማደጎዉ ግርግር

የፖፕ ሙዚቃ፣ ንግስት በመባል የምትታወቀዉ አሜሪካዊቷ Madonna

ማዶና በማላዊ ጉብኝቷ

ማዶና በማላዊ ጉብኝቷ

ባለፈዉ ሳምንት ከባለቤትዋ Guy Ritchie ጋር በመሆን አንድ የአስራ ሶስት ወር ህጻን ከማላዊ በማደጎ ወስዳለች።
በአለም እጅግ ደኸ ከሚባለዉት ሐገራት አንዷ ከሆነችዉ አፍሪቃዊቷ አገር፣ ከማላዊ የአስራ ሶስት ወራት እድሜ ያለዉን ህጻን በህግ ተፈቅዶላት እንደወሰደች ታዉቋል። ህጻን ዴቪድ ከተወለደ ከጥቂት ቀናት በኳላ እናቱ እንደሞተችበት እና ከናቱ ሞት በኳላ ወላጆቻቸዉን ያጡ ህጻናት በሚኖሩበት ጣብያ ይኖር እንደነበርም ታዉቋል። የታዋቂዋ ሙዚቀኛ ማዶና ህጻን ለማሳደግም ሆነ ለመርዳት፣ ከማላዊ መዉሰዶዋ፣ ሰሞኑን የአለምን ዜና መድረክ አጣቦአል። በርካታ በአለም ታዋቂ የፊልምም ሆነ የሙዚቃ ሰዎች፣ ህጻናትን ከአፍሪቃ በመዉሰድ የማሳደጉን ተግባር እንደ ልማድ የተያያዙት ይመስላል። እንደ ማላዊ ህግ ማንኛዉም አይነት የዉጭ አገር ዜጋ የማላዊ ህጻንን በጉዲፈቻነት መዉሰድ አይችልም።

ምክንያቱም አንድ ዜጋ ባህሉን አኗኗሩን ረስቶ መኖር የለበትም የሚል ህግ አላቸዉ፣ ይሁን እና ማዶና አንድ ህጻን ከማላዊ መዉሰዱዋ አነጋጋሪ ርዕስ ሆንዋል። የህጻኑ አባት Sky ለተባለዉ የብሪታንያ የዜና አዉታር እንደገለጸዉ፣ «ማዶና ህጻኑን አሳድገዋለሁ ስትል፣ እስከ መጨረሻዉ ልትወስደዉ ሳይሆን፣ እዚሁ ባለበት የምትረዳዉ መስሎኝ ነበር። እኔ ልጄን ለማደጎ ስሰጥ፣ የኔ ልጅነቱ እስከ ዘላለሙ የሚቀር መሆኑን የገለጸልኝ ሰዉ አልነበረም። እንዲህ መሆኑ ተነግሮኝ ቢሆን ኖሮ፣ በዚህ ጉዳይ አልስማማም ነበር። ይህን ጉዳይ በተመለከተ ተጨማሪ ማብራሪያ እንዲሰጠኝ እፈልጋለሁ። እኔ የምመርጠዉ ግን፣ ልጄ ተመልሶ እዚሁ ህጻናት ማሳደግያ ተቀምጦ ላየዉ መቻሌን ነዉ» ብሎአል። ከአራት ቀናት በፊት በአንጻሩ ማዶና ለልጁ ጥሩ ህይወትን ትሰጠዋለች ማለቱ ይታወሳል።

የ48 አመቷ ማዶና ከመጀመርያ እና ከሁለተኛ ታዳርዋ ያፈራቻቸዉ ሁለት ልጆች አልዋት። ማዶና ከማላዊ ስለወሰደችዉ ህጻን «ሲያድግ አንድ ቀን ወደ አገሩ መመለሱ አይቀሪ ነዉ፣ እራሱን ሲችል ምን ማድረግ እንደሚፈልግ እራሱ ይወስናል» ባይ ናት። የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅቶችም ማዶና በገንዘቧ ብቻ ከማላዊ ልጅ ለመዉሰድ ችላለች ብለዉ ድርጊቱን ነቅፈዋል።
በቅርቡ፣ የዩኤስ አሜሪካዊቷ፣ አንጀሊና ጁሊ፣ ከኢትዮጽያ አንዲት ህጻን በማደጎ መዉሰዷ ይታወሳል።

አዜብ ታደሰ

ተዛማጅ ዘገባዎች