ማየት የተሳነው ኢትዮጵያዊ ስደተኛ በሶማሊላንድ | ባህል | DW | 09.04.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

ማየት የተሳነው ኢትዮጵያዊ ስደተኛ በሶማሊላንድ

ማየት የተሳነው የ26 ዓመት ወጣት ስደተኛ ነው። ገና ዕውቅና ባላገኘችው ግን ራሷን ሐገር ብላ በሰየመችው ጎረቤት ሶማሊላንድ ውስጥ በስደት ሲባትት አራት ዓመታትን አስቆጥሯል። ታዲያ ተስፋ ያጣች መንፈሱን ዘወትር በብዕሩ ጠብታ በሚያፈልቃቸው የግጥም ሰንኞቹ ለማፅናናት ይሞክራል። በስደት ዓለም መከራ፦ ከአብራኩ የተከፈሉት ሁለቱ ብላቴናዎቹ

ማየት የተሳናቸው የብሬል መፃፊያ

ማየት የተሳናቸው የብሬል መፃፊያ

እንዲያ አብረውት የመጎሳቆላቸው ዕጣ ልቡን ሲያደማው ደግሞ፤ ለራሱ በሚያንጎራጉረው ዜማ ውስጡን ለማከም ይሞክራል። ከምንም በላይ ግን አድማጭ አጥተው በስደት አብረውት የሚንከራተቱ ግጥሞቹን የሚያደምጥለት ያገኘ ለት መንፈሱ ሠላም አግኝታ እንደምትረጋ ይገልፃል። ወጣቱን በስደት የሚኖርበት ሶማሊላንድ ደውዬ አነጋግሬዋለሁ። ግጥሞቹንም፣ የመሰደዱ ሰበብንም ያስደምጠናል። ለዝግጅቱ ማንተጋፍቶት ስለሺ ነኝ ፤አብራችሁን ቆዩ። ማንተጋፍቶት ስለሺ ሂሩት መለሰ